ያመለጥንበት የእግዚአብሔር ሕይወት

በተጨነቁ እና መከራ በበዛባቸው ጊዜ ወደ የተሰበሰቡት ወይም ያመለጡበት

 

የሐዋርያት ሥራ 7

11 በግብፅና በከነዓንም አገር ሁሉ ራብና ብዙ ጭንቅ መጣ፥ አባቶቻችንም ምግብን አላገኙም።

12 ያዕቆብም በግብፅ እህል መኖሩን በሰማ ጊዜ በመጀመሪያ አባቶቻችንን ሰደዳቸው፤

13 በሁለተኛውም ዮሴፍ ለወንድሞቹ ታወቀ፥ የዮሴፍም ትውልድ በፈርዖን ዘንድ ተገለጠ።

14 ዮሴፍም አባቱን ያዕቆብንና ሰባ አምስት ነፍስ የነበረውን ቤተ ዘመድ ሁሉ ልኮ አስጠራ።

 

  • የያዕቆብ ቤት ሁሉ የሄዱት ቀድሟቸው ወደ ግብጽ ወደ ገባው ወደ ዮሴፍ ነበር።

 

ኦሪት ዘጸአት 3

12 እርሱም፦ በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ነው ሕዝቡን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ ለእግዚአብሔር ትገዛላችሁ አለ።

 

  • ፈርዖን እስራኤልን ሁሉ የበኩር ልጆቻቸውን በመግደል ባስጨነቀ ጊዜ የወጡት በምድረ በዳ በነበረው በሙሴ አማካይነት ወደ ምድረ በዳ እግዚአብሔር ወዳለበት ነበር።

 

እግዚአብሔር ያስመለጠን እርሱ ወዳለበት ሕይወት ነው።

 

ወደ ቆላስይስ ሰዎች

1፥13-14 እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።

 

  • በሚመጣብን በማናቸው ነገር ሁሉ መጠጊያችን የእግዚአብሔር የራሱ ሕይወት ነው።

Print

የተሸነፈ ዓለም

ይህ ዓለም በክርስቶስ የተሸነፈ ነው!

የዮሐንስ ወንጌል 16፥33 በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።

Print

አይኖቻችንን በእግዚአብሔር ላይ እናድርግ

አሁን ያለንበት ጊዜ የሚያስፈራ ቢሆንም፤ እንደ ሁልጊዜውም ዓይኖቻችን በጌታ ላይ ናቸው። ነብዩ ኤርምያስ ይህ ስለገባው የደህንነቱን ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ አደርጎት ነበር።

Print

እግዚአብሔር ይግነንባችሁ

ኢየሱስ ኢየሱስ የሚሉ ሰዎች አጋጥመውህ ያውቃሉ? ይህን የሚሉት እርሱ ስለገነነባቸው ነው።

Print

እግዚአብሔር ከስምህ በላይ ነው

ከስምህ እና ከተጠራህበት አቅም በላይ እንድትኖር እግዚአብሔር ጠርቶኃል። ይህም ደግሞ የሚሆነው እግዚአብሔር በክርስቶስ የሰራልንን ስራ በማመን ብቻ ነው።

Print

በክርስቶስ መኖር

Print

በክርስቶስ መጽደቅ



ወደ ገላትያ ሰዎች 2፥17
"ነገር ግን በክርስቶስ ልንጸድቅ የምንፈልግ ስንሆን ራሳችን ደግሞ ኃጢአተኞች ሆነን ከተገኘን፥ እንግዲያስ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ነዋ? አይደለም።"

Print

ክርስቶስ ሰላማችን

ሰላማችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

Print

እረፍት!

Print

  • 1
  • 2

ይፈልጉ

ይግቡ