አይኖቻችንን በእግዚአብሔር ላይ እናድርግ

Written by Super User.

አሁን ያለንበት ጊዜ የሚያስፈራ ቢሆንም፤ እንደ ሁልጊዜውም ዓይኖቻችን በጌታ ላይ ናቸው። ነብዩ ኤርምያስ ይህ ስለገባው የደህንነቱን ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ አደርጎት ነበር።

 

ሰቆቃው ኤርምያስ 3፡24-26 "ነፍሴ፦ እግዚአብሔር እድል ፈንታዬ ነው፤ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ አለች። ጤት። እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው። ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።"

 

 

ኤርምያስ ለነፍሱ በእግዚአብሔር መታመንን እንዳስተማራት የእኛም ድርሻ እድል ፈንታችን በእግዚአብሔር ላይ መሆኑን ለነፍሳችን ማስተማር ነው፤ አይኖቻችንን በጌታ ላይ ብቻ እናደርጋለን፤ ምክንያቱ የእኛ ፍጻሜ ያለው በእግዚአብሔር እንጂ ጠላታችን በሚለው ላይ አይደለም። እግዚአብሔር ስለ እኛ መልካምን የሚያስብልን ደግሞም የሚያደርግልን ነው።

 

ትንቢተ ኤርምያስ 29፡11 "ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።"

እግዚአብሔር ስለ እኛ ክፉን አስቦ አያውቅም፤ አሳቡ ሁልጊዜ ለእኛ መልካም ነው።

Print