የተሸነፈ ዓለም

ይህ ዓለም በክርስቶስ የተሸነፈ ነው!

የዮሐንስ ወንጌል 16፥33 በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።

በዚህ ዓለም ሳለን መከራው አለ። ነገር ግን መከራው ያለው በአሸናፊነት ሳይሆን በተሸነፈ ማንነቱ ነው። ጌታ ሲናገር አይዟችሁ ያለው ዓለም በክርስቶስ የተሸነፈ በመሆኑ ነው። እኛም ደግሞ በክርስቶስ ስላለን በእርሱ አሸናፊዎች ነን። ስለዚህም ይህ ቃል ስላለን ሰላም አለን።

ዮሐንስ በመልእክቱ ደግሞ እኛም ይህንን ዓለም እንዳሸነፍነው ይነግረናል። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፥4 "ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና።" ዘራችን ከእግዚአብሔር ስለሆነ ይህንን ዓለም አሸንፈነዋል። ያሸነፈውም ደግሞ እምነታችን ነው። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፥4 “ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።”

ከእግዚአብሔር ስለተወለድክ ዓለምን አሸንፈኸዋል!

 

Print

ይፈልጉ

ይግቡ