ክርስቶስ ሰላማችን

ሰላማችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፥14-15 "እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥"

ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከእግዚአብሔር ጋር በማስታረቅ፣ የጥልን ግድግዳ በሥጋው በማፍረስ ከተስፋው ቃል ኪዳን ወራሾችና ከአህዛብ አንድን አዲስ ሰው በመፍጠር ደግሞም የራሱን ሰላም ሰጥቶን የውስጥ ሰላምን ያሳየን ሰላማችን ነው። ስለዚህም ከኢየሱስ የተነሳ ከእግዚአብሔር የታረቅን፣ ከሰዎች የታረቅን እናም ደግሞ ከራሳችን የታረቅን ነን።

እርሱ ሰላማችን ነው።

Print

ይፈልጉ

ይግቡ