• Home

በእውነትህ ቀድሳቸውየዮሐንስ ወንጌል 17፥17 በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው።

እግዚአብሔር የሚቀድሰን ወይም የሚለየን በቃሉ እውነት ነው። የእግዚአብሔር ቃል እውነት በሰው ልብ ውስጥ አድሮ የመለየትና የመቀደስ ብቃት አለው።

ብድራት ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉትወደ ዕብራውያን 10፡

32-33 ነገር ግን ግማሽ በነቀፋና በጭንቅ እንደ መጫወቻ ስለ ሆናችሁ ግማሽም እንዲህ ካሉት ጋር ስለ ተካፈላችሁ፥ ብርሃን ከበራላችሁ በኋላ መከራ በሆነበት በትልቅ ተጋድሎ የጸናችሁበትን የቀደመውን ዘመን አስቡ።

በጌታ ደስ ይበላችሁ

በጌታ ደስ ይበላችሁ ሲል ለምን እንዳለ ማወቁ በጣም ይረዳናል። ሰዎች የሚደሰቱት "ይህ አለን" ብለውና ይህን ያላቸውን ነገር በማሰብና በማሰላሰል ነው። ነቢዩ እንባቆምን በጽሑፉ ስናየው በህይወቱ ሲያስደስቱት የነበሩ ነገሮች ነበሩ።

የእግዚአብሔር ስም የጸና ግምብ ነው


መጽሐፈ ምሳሌ 18፥10 የእግዚአብሔር ስም የጸና ግምብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል።

የእግዚአብሔር ስም ለሚታመኑት በከፍታ እንደተሰራ የመጠለያ ግንብ ነው። ጠላት ያለውን ሁሉ ቢወረውር በዚህ ስም የተከለለውን ሊነካው አይችልም። ስሙ የጸና ግምብ ነው።

በከፍታ ስፍራ እንደተቀመጠ ሰው በዚህ ስም የተደገፈ ሁሉ እንደዚሁ በከፍታ ስፍራ ሆኖ ይጠበቃል። የጻድቅም ተስፋው የእግዚአብሔር ስም ነው። ጻድቅ ሁልጊዜ የሚሮጠው ወደ እግዚአብሔር ስም ነው።

 

  • 1
  • 2

ይፈልጉ

ይግቡ