መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 17

አሰላለፍሀን ቀይር፣

ፍልስጤም እንደ ተሰለፈ አትሰለፍ፣ ፍልስጤም እንደ ተከማቸ አትከማች፤

አምላክህ እግዚአብሔር የሚለካ አምላክ ስላልሆነ ... አምላክህን በእምነትህ አትወስነው፤

መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 21፡28 የእግዚአብሔርም ሰው ቀርቦ የእስራኤልን ንጉሥ፦ እግዚአብሔር
እንዲህ ይላል፦ ሶርያውያን፦ እግዚአብሔር የተራሮች አምላክ ነው እንጂ የሸለቆ አምላክ አይደለም
ብለዋልና ይህን ታላቅ ጭፍራ ሁሉ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ
ታውቃላችሁ አለው።

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፥3 ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን?

2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፥3 በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፥4 አንዱ፦ እኔ የጳውሎስ ነኝ፥ ሁለተኛውም፦ እኔ የአጵሎስ ነኝ ቢል ሰዎች ብቻ መሆናችሁ አይደለምን?


11 ሳኦልና እስራኤልም ሁሉ እንዲህ የሚላቸውን የፍልስጥኤማዊውን ቃል በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፥
ደነገጡም።

ከሰሙት ቃል የተነሳ ፈሩት

23 እርሱም ሲነጋገራቸው፥ እነሆ፥ ጎልያድ የተባለው ያ ዋነኛ ጀግና ፍልስጥኤማዊ የጌት ሰው
ከፍልስጥኤማውያን ጭፍራ መካከል ወጣ፥ የተናገረውንም ቃል ተናገረ ዳዊትም ሰማ።

16 ፍልስጥኤማዊውም ጥዋትና ማታ ይቀርብ፥ አርባ ቀንም ይታይ ነበር።

ሰይጣን ቃሉን በመደጋገም ያምናል፤ ምክንያቱም ደጋግመህ የሰማኸው ነገር ተጽእኖ አለው፤ ስሜትህን የሚቆጣጠረው የምታውቀው ነገር ሳይሆን፤ የደጋገምከው ነገር ነው ስሜትህ ለሚደጋገምለት ነገር ተገዥ ነው ደጋግመህ የምትሰማው ቃል ይገዝፍብኃል፤ ስጋ ይለብስብሃል ስለዚህ ነው እግዚአብሔር ለኢያሱ ይከናወንልህ ዘንድ ይህንን የመጽሐፍ ቃል በቀንም በለሊትም አስበው ያለው።

መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1፡8 የዚህ ሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ፥ ነገር ግን የተጻፈበትን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ በቀንም በሌሊትም አስበው፤ የዚያን ጊዜም መንገድህ ይቀናልሃል ይከናወንልሃልም።

ከዚህ ድምጽ መራቂያ

  1. ከዚህ ድምጽ ኢንቫይሮመንት ዞር በል
    28 ታላቅ ወንድሙም ኤልያብ ከሰዎች ጋር ሲነጋገር ሰማ፤ የኤልያብም ቍጣ በዳዊት ላይ ነድዶ፦ ለምን ወደዚህ ወረድህ? እነዚያንስ ጥቂቶች በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውሃቸው? እኔ ኵራትህንና የልብህን ክፋት አውቃለሁና ሰልፉን ለማየት መጥተሃል አለው።
    29 ዳዊትም፦ እኔ ምን አደርግሁ? ይህ ታላቅ ነገር አይደለምን? አለ።
    30 ዳዊትም ከእርሱ ወደ ሌላ ሰው ዘወር አለ፥ እንደዚህም ያለ ነገር ተናገረ፤ ሕዝቡም እንደ
    ቀድሞው ያለ ነገር መለሱለት። ዳዊት ከሚሰማው የወንድሙ ድምጽ ዘወር አለ። ስለ አንተ የእግዚአብሔር ቃል ከማይናገረው ነገር ጋር አትቆይ፤ ዞር በል። አቢጋይል ዳዊትን በልብህ አታኑረው አለችው

የምታምሰለስለው ድምጽ አንተን ለመግዛት አቅም አለው። አንዳንድ ክርስቲያኖች የጌታን ታላቅነት እያወቁ፣ ስሜታቸውና ፈቃዳቸው ግን የተሸነፈ ይሆንባቸዋል፤ ስሜትህ እና ፈቃድህ የተገዛብህ ለእውቀትህ ሳይሆን ለተደጋገመብህ ነገር ነው፤ ላምሰለሰልከው፤ ምስል ለሰራብህ ነገር ነው።

የሉቃስ ወንጌል 8፥18 እንግዲህ እንዴት እንድትሰሙ ተጠበቁ፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና፥ ከሌለውም ሁሉ፥ ያው ያለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።

የማርቆስ ወንጌል 4፥24 አላቸውም፦ ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ። በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል ለእናንተም ይጨመርላችኋል።

2. ጸሎት እና ኮንፌሽን
ዳዊት ስለ ጎልያድ በመዝሙሩ ሲናገር እንዲህ አለ
መዝሙረ ዳዊት 144፥7-8 እጅህን ከአርያም ላክ አድነኝም ከብዙ ውኆች፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር፥ ቀኛቸው የሐሰት ቀኝ ከሆነ፥ ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ።

144፥11 አድነኝ፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር፥ ቀኛቸውም የሐሰት ቀኝ ከሆነ፥ ከባዕድ ልጆች እጅ
አስጥለኝ።

ዳዊት አፋቸው እርግማንን ከሚያወሩ፣ ከነጎልያድ አስጥለኝ አለ፤
በልሳን የሚጸልይ ሰው ከዚህ ዓይነት ነገር ራሱንና ኃሳቡን ያነጻል
እሱ ብቻ ሳይሆን ኮንፌሽንህን ቀይረው

መዝሙረ ዳዊት 144፡12 ልጆቻቸው በጕልማስነታቸው እንደ አዲስ አትክልት የሆኑ፥ ሴቶች
ልጆቻቸውም እንደ እልፍኝ ያማሩና ያጌጡ፤
13 ዕቃ ቤቶቻቸውም የተሞሉ በየዓይነቱ ዕቃ የሚሰጡ፥ በጎቻቸውም ብዙ የሚወልዱ፥
በማሰማርያቸውም የሚበዙ፥
14 ላሞቻቸውም የሚሰቡ፤ ቅጥራቸውም መፍረሻና መውጫ የሌለው፥ በአደባባዮቻቸውም
ዋይታ የሌለ፤
15 እንደዚህ የሚሆን ሕዝብ የተመሰገነ ነው፤ እግዚአብሔር አምላኩ የሆነ ሕዝብ ምስጉን ነው።
ኮንፌሽንህ ካውንተር ማድረጊያም ነው፤

ዳዊት ሰምቶ ብቻ የጎልያድን ድምጽ ብቻ ሰምቶ አልሄደም፤ ነገር ግን የተናገረውን ቃል በቃል ሻረው። ዳዊት ለፍልስጥኤማዊው መልስን መልሶለት ነበር ጌታ ኢየሱስ በተፈተነበት ጊዜ ሁሉ መልስን መልሶ ነበር መዋጊያ መሳሪያችን የእግዚአብሔር ቃል ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ የሚወጋው
በአንደበታችን ስንናገረው ነው።

ለየት ያለ ቃል ሲኖርህ ሬኮግናይዝ ትደረጋለህ፤
31 ዳዊትም የተናገረው ቃል ተሰማ፥ ለሳኦልም ነገሩት፤ ወደ እርሱም አስጠራው። የምትናገረው ቃል ላንተ ብቻ ሳይሆን ከአንተ ጋርም አብሮህ ተሰልፎ ለወጣው ነው። ለጎልያድ የተናገረውን ቃል ብናየው፤ ዳዊት እየተናገረ የነበረው ለጎልያድ ብቻ አልነበረም ነገር ግን ለእስራኤላውያንም ጭምር እንጂ። ለጎልያድ የተነገረውን ለእስራኤልም ማለት የሚችለው ቃል ነው፤

መዝሙረ ዳዊት 124
የዳዊት የመዓርግ መዝሙር።
1 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል፦
2 እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥
3 ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤
4 በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ፈሳሽ ባለፈ ነበር፤
5 በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር።
6 ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ።
7 ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች፤ ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን።
8 ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በእግዚአብሔር ስም ነው።

3. መታሰብ ያለበትን ማሰብ
መጽሐፈ ነህምያ 4፥14 አይቼም ተነሣሁ፥ ታላላቆቹንና ሹማምቱንም የቀሩትንም ሕዝብ፦ አትፍሩአቸው
ታላቁንና የተፈራውን ጌታ አስቡ፥ ስለ ወንድሞቻችሁም ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች
ልጆቻችሁም ስለ ሚስቶቻችሁም ስለ ቤቶቻችሁም ተዋጉ አልኋቸው።

ሰንባላጥና ጦቢያ የሚሉትን ከታስብና ከምታምሰለስል ታላቁንና የተፈራውን ጌታ አስበው፤
የእግዚአብሔርን ታላቅነት አውራው፤ ተናገረው

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4፥8 በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፥ ጽድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ንጹሕ የሆነውን ነገር ሁሉ፥ ፍቅርያ ለበትን ነገር ሁሉ፥ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፥ በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፥ እነዚህን አስቡ፤

ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፥2 በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም።

ወደ ዕብራውያን 12፥3 በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኃጢአተኞች በደረሰበት እንዲህ
ባለ መቃወም የጸናውን አስቡ። 

4. የእግዚአብሔር ቃል ሙላት ይኑርብህ

የእግዚአብሔር ቃል ሙላት ማለት ሽምደዳ ማለት አይደለም።
የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ ማለት፤ የቃሉ ብርሃን ይብራላችሁና ተጽኖ
ያሳድርባችሁ ማለት ነው።

ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3፥16 የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤