ትንቢተ ኢሳይያስ 8፥11 እግዚአብሔርም በጽኑ እጅ እንዲህ ተናገረኝ፥ በዚህም ሕዝብ መንገድ አንዳልሄድ አስጠነቀቀኝ፥ እንዲህም አለኝ፦ 12 ይህ ሕዝብ፦ ዱለት ነው በሚሉት ሁሉ፦ ዱለት ነው አትበሉ፤ መፈራታቸውንም አትፍሩ፥ አትደንግጡ። 13 ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት፤ የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን።

እግዚአብሔር የገነነበት ሰው የሚፈራው አያስፈራውም፤ ሰው የሚያስደነግጠው ነገር አያስደነግጠውም። የገነነበት የእግዚአብሔር ማንነት ብቻ ስለሆነ። ኢሳይያስንም እግዚአብሔር በብርቱ ያስጠነቀቀው ነገር ቢኖር ሰው እንደሚመልሰው ምላሽ ነገርን እንዳይመልስ ነው፤ ሰው እንደሚናገረውም ደግሞ እንዳይናገር ነው፤ እግዚአብሔር ብቻ እንዲገንበት።

ሕዝብ ከተናገረው ወይም ከሚፈራው እና ከሚደነግጥለት ነገር ይልቅ የእግዚአብሔር ማንነት ይግነንብን።

እግዚአብሔር የገነነበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ያስባል፤ የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል፤ የእግዚአብሔርን ቃል ይኖራል። 

መዝሙረ ዳዊት 119፥23 አለቆች ደግሞ ተቀምጠው እኔን አሙኝ፤ ባሪያህ ግን ሕግህን ያሰላስል ነበር።