ከቃሉ
- Details
- Category: ከቃሉ
ክርስቶስ የመጣው ሊያሳርፈን ነው። እኛ ልንፈጽመው ያልቻልነውን የጽድቅን ሥራ እርሱ ፈጽሞልን በእኛ ላይ የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደምስሶታል። ይህም የዕዳ ጽሕፈት ይቃወመን እና ይከሰን የነበረ ትእዛዝ ሲሆን ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀሉ ስራ ከመንገዳችን ላይ አንስቶታል። ስለዚህም ዳግመኛ በዚህ ትእዛዝ ላንያዝ ዘንድ ነጻ ወጥተናል። ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ተሰቅሎ፣ ሞቶ፣ ተቀብሮ ደግሞም ከሙታን ተነስቶ ወደ ነጻነታችን አስገብቶናል። እንኳን በክርስቶስ ኢየሱስ ወደዚህ የእረፍት ነጻነት መጡ። ክብር ለስሙ ይሁን።
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡14 በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤
- Details
- Category: ከቃሉ
እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ የእርሱን ህይወት ተካፋዮች እንዲሆኑ ጠርቷቸዋል። ይህም ጥሪ በወንጌል እውነት በኩል የሚሆን የመዳንና ህይወትን የመካፈል ጥሪ ነው።
ወደ ዕብራውያን 3፥1 ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ
- Details
- Category: ከቃሉ
የያዕቆብ መልእክት1፥17 በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
እግዚአብሔር የበጎ ስጦታ ሁሉ ደግሞም የፍጹም በረከት ሁሉ መገኛ ነው። የሚሰጠውም ከማንነቱ የተነሳ ነው፤ ይህም ማንነቱ ፍቅር ነው። ይህ ፍቅር የሆነው አምላክ በሚለዋወጥ ነገር የማይለዋወጥ፤ በሚቀያየርም ሁነት የማይቀያየር ፍጹም የሆነ አምላክ ነው።
የእግዚአብሔር ስጦታ በጎ ነው፤ እግዚአብሔር ክፉን አይሰጥም፤ ከእርሱ ዘንድ ክፉ አይወርድም። ነገር ግን በጎ የሆነው አምላክ ለሰው ልጆች ሁሉ በጎን ነገር ማድረግ ይወዳል። ስለዚህም የበጎነት መገለጫው የሆነውን ልጁን ሰጥቶናል። ስለዚህም የእርሱን በጎነት እናወራለት ዘንድ በልጁ በኩል ልጆቹ አድርጎ ባርኮናል። እግዚአብሔር የሰጠው ትልቁ የበጎነቱ ስጦታ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ እርሱንም በማመን ያገኘነው ልጅነት የእግዚአብሔር በጎነት ነው። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2፥9
እግዚአብሔር የባረከንም በረከታችን ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በእርሱ ሆነን በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ ተባርከናል። ይህም በረከታችን እንከን የማይወጣለት፣ የማይጨመርበት ፍጹም የሆነ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ሳይሰስት፣ ሳያስለምን፣ ሳያጎድል የባረከን እግዚአብሔር ይባረክ።