በሚበልጥ ክብር መገለጥ

በዘመናችን እየታየ ያለው እንቅስቃሴ በተለይ ከእግዚአብሔር ቃል አኳያ የምናያቸው አብዛኞቹ ነገሮች አሳዛኝ፣ ልብ ሰባ፣ አስከፊ እና ፀያፍ ናቸው። ክርስቲያን እንደ ክርሰቲያንነት የሚታይበት የሌለው፣ እግዚአብሔርን እከተላለሁ የሚል እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የማይሄድ የበዛበት ዘመን፣ ከተግባራዊ ክርስትና ይልቅ አፋዊ ክርስቲያን እና ክርስትና እያየን ያለንበት ዘመን፣ ለአብነት ምስክር መሆን የማንችል፣ ለሌሎች ለሚያምኑም ይሁን ለማያምኑ መልካም ምስክርነት የሌለን ተላላዎች ሆነን እየታየን ነው። ይህ ማንነት ግን ጨርሶ እግዚአብሔራዊ እና ክርስቶሳዊ እና ክርስቲያናዊ አይደለም። ከጥንት የነበሩ በመጽሐፍ ቅዱስ ያየናቸው የእግዚአብሔር ሰዎች በዚህ ማንነት ተገልጠው አናያም፣ ይልቁኑ መንግስታትን በጽድቅ ኖረው፣ አገልግለው ድል ነስተው እግዚአብሔርን አስከብረው አልፈዋል። በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ይሁኑ በእግዚአብሔር ነገር እና ጉዳይ አይደራደሩም፣ እስከመጨረሻው በእግዚአብሔር ጉዳይ ይጋፈጣሉ፣ ይወራረዳሉ በመጨረሻም በእግዚአብሔር ያሸንፋሉ። በሚበልጥ ክብር፣ በሚበልጥ በእግዚአብሔር ኃይልና ክብር መገለጥ በዘመኑ ላይ ባለው ክፋት፣ አመፅ፣ ከእግዚአብሔር በተቃራኒ በቆመ ላይ አይሎ፣ ረግጦ፣ አሸንፎና አጥፍቶ በበላይነት በመቆም የእግዚአብሔርን ስም እንዲገን በማድረግ በገዢነት ለመቆየት ወሳኙ ነው። በተለይ የቀደሙት የእምነት አባቶች በምርኮ ዘመን ላይ ተላልፈው ለጠላት በተሰጡበት ዘመን በምርኮ ሐገር የገዛቸውን አሸንፈው የኖሩት በእግዚአብሔር ላይ ባላቸው እምነት፣ በዘመናቸው እየገዛቸውና ልግዛቸው ያለውን አሸንፈው፣ ረትተው የተገኙ በላያቸው ባለው በተገለጠው በእግዚአብሔር ክብር ነው። እግዚአብሔርን አሳይተው፣ አስከብረው፣ በእውነትም የእነርሱ አምላክ በእርግጥም አምላክ ነው አሰኝተው የኖሩት በላያቸው ባለው የእግዚአብሔር ክብር፣ በኖሩለት እግዚአብሔር በምርኮ ሀገር አሸንፈዋል፣ ይህም በተወራረዱበት በእግዚአብሔር ኃይል ነው። በዘመናቸው ላይ ተጽዕኖ ፈጥረው፣ አሳድረው በዘመናቸው ላይ በበላይነት በአሸናፊነት ኖረዋል።

በበብሉይ ኪዳን የነበረው የእግዚአብሔር ክብር ሲገለጥ 

1- ሙሴና አሮን

የአስማተኞችን በትር፦ “እግዚአብሔርም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ተናገራቸው፦”   — ዘጸአት 7፥8። “ፈርዖን፦ ተአምራትን አሳዩኝ ሲላችሁ፥ አሮንን፦ በትርህን ወስደህ እባብ እንድትሆን በፈርዖን ፊት ጣላት በለው።” — ዘጸአት 7፥9። “ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ እግዚአብሔርም እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በፈርዖንና በባሮቹ ፊት ጣለ፥ እባብም ሆነች።” — ዘጸአት 7፥10። “እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፥ እባቦችም ሆኑ፤ የአሮን በትር ግን በትራቸውን ዋጠች።” — ዘጸአት 7፥12።

2- ኤሊያስ

“ኤልያስም፦ እስራኤልን የምትገለባብጡ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ በኣሊምን የተከተላችሁ፥ አንተና የአባትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔ አይደለሁም።”— 1ኛ ነገሥት 18፥18። “አሁንም ልከህ እስራኤልን ሁሉ፥ በኤልዛቤልም ማዕድ የሚበሉትን አራት መቶ አምሳ የበኣልን ነቢያት፥ አራት መቶም የማምለኪያ ዐፀድን ነቢያት ወደ እኔ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብ አለ።”   — 1ኛ ነገሥት 18፥19። “የእግዚአብሔርም እሳት ወደቀች፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕቱንም እንጨቱንም ድንጋዮቹንም አፈሩንም በላች፥ በጕድጓዱም ውስጥ ያለውን ውኃ ላሰች።” — 1ኛ ነገሥት 18፥38። “ኤልያስም፦ ከበኣል ነቢያት አንድ ሰው እንዳያመልጥ ያዙ አላቸው። ያዙአቸውም ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ በዚያ አሳረዳቸው።”   — 1ኛ ነገሥት 18፥40። “አክዓብም ሊበላና ሊጠጣ ወጣ፤ ኤልያስም ወደ ቀርሜሎስ አናት ወጣ፤ ፊቱንም በጕልበቱ መካከል አድርጎ በግምባሩ ተደፋ።”   — 1ኛ ነገሥት 18፥42።

በአዲስ ኪዳን የነበረው የእግዚአብሔር ክብር ሲገለጥ

  1. ኢየሱስ ክርስቶስ:-  ተአምራቱ: ፈውስ፣ ሙታንን ማንሳት፣ ተፈጥሯዊ ነገሮችን መቆጣጠር ጥቅስ: “ኢየሱስም በከተሞችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር… ሕመምና ድካም ሁሉ ይፈውስ ነበር።” “ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።”— ማቴዎስ 4፥23። “ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፥ ፈወሳቸውም።”   — ማቴዎስ 4፥24። “ከገሊላም ከአሥሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።” — ማቴዎስ 4፥25። “ዕውሮች ያያሉ አንካሶችም ይሄዳሉ፥ ለምጻሞችም ይነጻሉ ደንቆሮችም ይሰማሉ፥ ሙታንም ይነሣሉ” — ማቴዎስ 11፥5።
  2. ሐዋርያ ጴጥሮስ “ጴጥሮስ ግን፦ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።”   — ሐዋርያት 3፥6። “ወደ ላይ ዘሎም ቆመ፥ ይመላለስም ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደ መቅደስ ገባ።” — ሐዋርያት 3፥8። “ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ሲመላለስ አዩት፤”   — ሐዋርያት 3፥9። “መልካምም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ ስለ ምጽዋት ተቀምጦ የነበረው እርሱ እንደ ሆነ አወቁት፤ በእርሱም ከሆነው የተነሣ መደነቅና መገረም ሞላባቸው።” — ሐዋርያት 3፥10። “ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፥ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ፦ ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች።”   — ሐዋርያት 9፥40። “ይህም በኢዮጴ ሁሉ የታወቀ ሆነ፥ ብዙ ሰዎችም በጌታ አመኑ።”   — ሐዋርያት 9፥42።
  3. ሐዋርያ ጳውሎስ ተአምራቱ: ፈውስ፣ ክፉ መናፍስት ማውጣት፣ ሙታን ማንሳት ጥቅስ: “እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ ያልተለመዱ ተአምራት ያደርግ ነበር።” ሐዋርያት 19፥11 “ጳውሎስም ተዘርግቶ ወደ እርሱ ወደቀ… ሕይወቱ በእርሱ ውስጥ ነው።” ሐዋርያት ሥራ 20፥10
  4.  ፊልጶስ (ወንጌላዊ) ተአምራቱ: ክፉ መናፍስት ማውጣት፣ ፈውስ ጥቅስ: “ክፉ መናፍስት በታላቅ ድምፅ እየጮኹ ይወጡ ነበር… ብዙ ሽባዎችና አካል ጉዳተኞች ፈወሱ።”ሐዋርያት ሥራ 8፥7
  5. እስጢፋኖስ ተአምራቱ: ታላቅ ድንቅና ምልክት ጥቅስ: “እስጢፋኖስም በጸጋና በኃይል ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ታላቅ ድንቅና ምልክት ያደርግ ነበር።” ሐዋርያት 6፥8
  6. ሐዋርያት በአጠቃላይ ተአምራቱ: ብዙ ምልክቶችና ድንቅ ሥራዎች ጥቅስ: “በሐዋርያት እጅ ብዙ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች በሕዝቡ መካከል ይደረጉ ነበር።”ሐዋርያት 5፥12

በአጠቃላይ፦ እነዚህ ተአምራት፦ 

  1.  ወንጌልን ለማረጋገጥ
  2. የእግዚአብሔር ኃይል ለማሳየት
  3. ሰዎችን ወደ እምነት ለመመራት

አገልጋይ በረከት ሱላሞ ሱጌቦ

+251902910126