yegizewkal
ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ትንቢተ ኤርምያስ 15፥16

  • Home/መነሻ ገጽ
  • Gospel Thoughts/የወንጌል አስተምህሮ
    • ነገረ ድነት/Salvation
  • The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
    • Literature/ስነ-ጽሑፍ
    • ከመጽሐፍት ዓለም
  • Churches/ቤተ ክርስቲያን
    • Religious News/ሐይማኖታዊ ዜና
  • Testimony/ምስክርነት
  • ማስታወቂያ/Advertisement
  1. You are here:  
  2. Home
  3. Gospel Thoughts/የወንጌል አስተምህሮ

Gospel Thoughts/የወንጌል አስተምህሮ

ጸሎት

Details
Written by: Bereket Sulamo
Category: Gospel Thoughts / የወንጌል አስተምህሮ

በምድር ላይ ካሉ ሐይማኖታዊ ነክ ከሆኑ እምነቶች አንዱ ክርስትና ነው። ክርስትና በባህሪው ዋነኛ አድርጎ ከሚንቀሳቀስባቸው አብይ ሚስጥራት መካከል አንዱ ጸሎት ነው። ጸሎት ለክርስቲያኖች የሁልጊዜ የማይቋረጥ ተግባራቸውና ስራቸው ነው። ሳይከውኑት የሚውሉት ወይም የሚያድሩት ጉዳይ አይደለም።

ጸሎት በሚጸልየውና ጸሎትን በሚሰማው በእግዚአብሔር መካከል ያለን ቁርኝት ማሳያ እና ማመልከቻ ነው።

ጸሎት በውስጡ የሚያካትታቸው አቢይ ጉዳዮች፥ ምስጋና፣ ልመና፣ ምልጃ እና በአጠቃላይ እነዚህን አካትቶ አምልኮ ነው። 

ጸሎት የሰው ልጅ የማይችለውን ጉዳይ እግዚአብሔር አንተ ትችላለህ ብሎን ልመናን ማቅረቢያ መንገድ ነው። ያለ ጸሎት ክርስትና አይታሰብም፣ ሊነጣጠልም የሚችል ጉዳይ አይደለም። 

ጸሎት ከሚደረግባቸው አይነቶች መካከል፦

1- በግል ሊቀርብ የሚችል፦ በተናጠል

2- በቡድን የሚቀርብ፦ በማህበር

3- በባለትዳሮች የሚቀርብ፦ የራሳቸውን ጊዜና ቦታ በመውሰድ

4- እንደ ሃገር የሚቀርብ፦ ለድንገተኛ ጥሪ ሲሆን (እግዚዮታ)

5- በቤተክርስቲያን፦ ለአማኞች የአንድነት ጊዜ ሲኖር የሚደረጉ የጸሎት አይነቶች ናቸው።

በተለይ ክርስቲያን የጸሎት ምንነትን እና እንዴትነት የጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልንማር የግድ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአርባ ቀናት ያህል ባለማቋረጥ ጸልዮአል። ለጸሎትም ይተጋ ነበር። የሉቃስ ወንጌል 22:39-49 (መከራው፣ ጽዋው እንዲያልፍ ጸለየ)

ጸሎት የልባችንን መሻት የምንለምንበት ዋነኛ መንገድ ነው። መዝሙረ ዳዊት 37:4

ምኞታችንን ከበረከቱ እንዲያጠግበን የምንለምንበት ነው። መዝሙረ ዳዊት 103:5

1- ጸሎት ልናበዛው የሚገባን ነው፦ ምናሳንሰው አይደለም

የምንፈልገውን ከእግዚአብሔር እስከምናገኝ ድረስ የምንከውነው ሥራ ነው፣ የምንፈልገውን እስከምናገኝ  አብዝተን ልናደርገው የሚገባ ነው።

ጸሎትዋንም በእግዚአብሔር ፊት ባበዛች ጊዜ ዔሊ አፏን ይመለከት ነበር። 1ኛ ሳሙኤል 1:12

2- በልብ የምንናገረው ነው፦ ሚስጢር ነው

ድብቅ የሆነን ለእግዚአብሔር ብቻ የምንነግረው ነው። ማንም ሊሰማው የማይገባ ነገራችንን የምንገልጽበት ነው። ሐናም በልብዋ ትናገር ነበር፤ ድምፅዋም ሳይሰማ ከንፈርዋን ታንቀሳቅስ ነበር፤ ኤሊም እንደ ሰከረች ቆጠራት። 1ኛ ሳሙኤል 1:13

3- የምንጮኸው ነው፦ ጉዳያችንን አበክረንና አጽንኦት ሰጥተን የምናቀርበው ነው

ወደ እግዚአብሔር የምንጮኸው፣ እግዚአብሔርም የሚመልስበት አቀራረብ ነው። ክርስቲያን አንዳች የሚደንቅን ነገር የሚፈልግ ነው። ለዚህም ነው እግዚአብሔር እንደ ትዕዛዝ የሚነግረን። "ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ሃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ። ትንቢተ ኤርምያስ 33:3

4- ጸሎት በትጋት ይደረጋል

ጸሎት አንዴ ሲመቸን፣ አንዴ ሳይመቸን የምናደርገው አይደለም። በምቾትም ይሁን በማይመች ሁኔታና ጊዜ የምናደርገው አይደለም። የእኛን ያለመድከም ይፈልጋል።

ጸሎት በብርታት ጊዜ የምንተወው፣ በድካም ጊዜ የምንቀጥለው አይደለም። ከሁኔታ ያለፈ ነው። በሁኔታም የሚወሰን፣ ወይም የሁኔታ ጥገኛ አይደለም። በምንም ሁኔታ እንሁን የምንተወው አይደለም። ስለዚህ፦ "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው። ማቴዎስ 26:41።

ወደ ደቀመዛሙርት መጣ፤ ተኝተውም አገኛቸውና ጴጥሮስን፦ እንዲሁም ከእኔ ጋር አንዲት ሰዓት እንኳ ልትተጉ አልቻላችሁምን? ማቴዎስ 26:40

5- ጸሎት ያለማቋረጥ የሚደረግ ነው

አንድ ወቅት ጸልየን በሌላ ቀን የምንተወው አይደለም፣ ጸሎት የሁልጊዜ ሥራችን ነው፣ ከእግዚአብሔር ጋር የምንነጋገርበት ነው። ስለዚህ ልናቋርጠው የሚገባን አይደለም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በኖረበት ጊዜ ከከወናቸው ድርጊቶች አንዱ ባለማቋረጥ መጸለዩ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለን፦ ሳታቋቂጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና። 1ኛ ተሰሎንቄ 5:17-18።

የቀደሙ አባቶችና ጸሎት

የቀደሙ አባቶች ከጸሎት ጋር የጠነከረ ቁርኝት አላቸው። ጸሎት እጅግ በእነርሱ ህይወት ውስጥ የተጣበቀ ነው። በጸሎት አይደራደሩም፣ ወደ ኋላም አይሉም፣ ጸሎት ልማዳቸው ነው። በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ይገኙ ጸሎትን አያቋርጡም።

1- አብርሃም፦ የእምነት አባት

በአብርሃም ሚስት በሣራ ምክንያት በአቢሜሌክ ቤት ማህፀኖችን ሁሉ ዘግቶ ነበርና አብርሃም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ሁሉም ተፈወሱ ወለዱም።  ዘፍጥረት 20:17-18

2-ይስሐቅ፦ ለአባቱ አብርሃም የታዘዘ

ስለ ሚስቱ መካንነት ጸለየ፣ እርሷም ፀነሰች። መካንነቷ ቀረ፣ ተወገደ፣ ዘር ተተካ። ዘፍጥረት 25:21

3- ሙሴ፦ ቁጣ እንዲመለስ ጸለየ

እግዚአብሔር በሕዝቡ ኃጢአት ምክንያት በመቆጣቱ፣ ቁጣው በመንደዱ ምክንያት እግዚአብሔር ከቁጣው  እንዲመለስ እግዚአብሔርን ይለምን ይጸልይ ነበር። ዘጸአት 8:30፤ ዘኁልቁ 11:2፤ 21:8።

4- ሃና፦ የስለት ጸሎት

ሃና በማህፀኗ መዘጋት፣ በመሃንነት የተነሳ በጣውንቷ ማስቆጣት ተበሳጭታ ወደ እግዚአብሔር የስለት አዘል ጸሎት ጸለየች፣ እግዚአብሔርም ሰማት፣ ልጅም አገኘች በስለቷም መሠረት ለእግዚአብሔር መልሳ ሰጠች። ስለት አዘል ጸሎት አቀረበች። 1ኛ ሳሙኤል 1:10፤ 1:12-14።

5- ኤልሳዕ- ሙት ህፃን በእጁ ተፈወሰ

ኤልሳዕ ሁሉን ወደሚችል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ የሞተውም ህፃን በእጁ እግዚአብሔር አስነሳው። 2ኛ ነገሥት 4:30-34፤ 6:18።

ስለዚህ ጸሎት ከእኛ ከክርስቲያኖች ተነጥሎ፣ ተለይቶ የሚታይና የሚገኝ አይደለም። ጸሎት ለክርስቲያኖች ወሳኝ ጉዳይ ነው።

ስለዚህ የጸሎት ጊዜና ቦታ በተለይም የጸሎት መሰዊያ ሊኖረን ይገባል። የጸሎት ጊዜና ቦታ ይኑረን፣ የጸሎት መሠዊያን እናበጅለት። 

የቀደሙት የእምነት አባቶች ከሚለዩባቸው ባህሪያት አንደኛው መለያ ባህሪያቸው በጸሎት ማመንና የጸሎት ስፍራ ማበጀትና ማዘጋጀታቸው ነው።

ከፊታችን ትልልቅ ፈተናዎች ይመጣሉ ይህንንም የምናልፈው በጸሎት ብቻ ነው። እግዚአብሔርን በማነጋገር። 

ጸሎት በእግዚአብሔር ፊት ሆነን እጅግ ትንሽ ጊዜን በመውሰድ የምንለምንበት፣ እጅግ ብዙ ከእግዚአብሔር የምንሰማበት ነው።

በመጨረሻም፦ "... የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።" ያዕቆብ 5:16

ስለዚህ ቅዱስ ሁሉ በምቹ ጊዜ ወደ አንተ ይለምናል፤ ብዙ የጥፋት ውኃም ወደ እርሱ አይቀርብም። መዝሙር 32:6።

አቤቱ፥ በመልካሙ ጊዜ ጸሎቴ ወደ አንተ ነው፤ አቤቱ በምህረትህ ብዛት በማዳንህም እውነት አድምጠኝ። መዝሙር 69:13

ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። ማቴዎስ 7:7።

ተባረኩ

አገልጋይ በረከት ሱላሞ ሱጌቦ

ፍጹምነትን መያዝ (INTEGRITY, JUSTIFICATION, PERFECTION)

Details
Written by: Bereket Sulamo
Category: Gospel Thoughts / የወንጌል አስተምህሮ

ክርስትና በእግዚአብሔር ፊት በምመካድ፦ለሰው ህይወትና መስተጋብር የምንገልጸው ሕይወት ነው። እግዚአብሔር የሚጠላውን ጠልተን፣ እግዚአብሔር የሚወደውን ወድደን እግዚአብሔርን እያስደሰትን የምንኖረው ሕይወትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ነው። 

Read more: ፍጹምነትን መያዝ (INTEGRITY,...

Subcategories

ነገረ ድነት/ Salvation

  • የአንደኛ ዮሐንስ መልዕክት
  • የአንደኛ ዮሐንስ መልዕክት
  • ጊዜ
  • ትጋት
  • ሐሰት፣ ሐሰተኛ፣ ሐሰተኝነት እና መገለጫቸው

Article Categories

  • Literature/ስነ-ጽሑፍ
  • Gospel Thoughts / የወንጌል አስተምህሮ
  • The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
  • Testimony/ምስክርነት
  • Religious News/ሐይማኖታዊ ዜና
  • Churches/ቤተ ክርስቲያን

Login Form

  • Forgot your password?
  • Forgot your username?
Copyright © 2025 yegizewkal. All Rights Reserved.