The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
- Details
- Written by: Bereket Sulamo
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
በመከራ ውስጥ የሚፀና ማንነት
“በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።” — ዮሐንስ 16፥33።
በአለም ስላለን ብቻ እኛ ክርስቲያኖች መከራ ይደርስብናል ማለቱ ተላላነት ነው፣ በአለም መኖሩ ሳይሆን ክርስቲያን መከራ የመጣበት በአለም ሳለን በእውነት በክርስቶስ ስላለን ነው። በእርግጥ የክርስቶስ ተከታይ ክርስቲያን መባሉ እንዳለ መከራ ቢያመጣም በእርሱ ካለን፣ እንደ ቃሉ ፈቃድ ስንኖር፣ የቃሉን ፈቃድ ስንፈፅም፣ ቃሉን ስንተገብር፣ የኃጢአትን መንገድ ጠልተን በክርስቶስ መንገድ መሄድ በእነዚህ ምክንያት እጅግ የበዛ መከራ መድረሱ አይቀሬ ነው።
በእርግጥ መከራ ፅናትን፣ ትዕግስትን፣ አቋምን የሚፈታተን ቢሆንም በፈተና ውስጥ መፅናቱ የመጨረሻ ዋጋው እጅግ የከበረ ነው። መከራ በዋናነት ከቆምንበት አቋም መጣል አሊያም ማስጣል፣ ከእግዚአብሔርም ጋር የነበረንን ብርቱ ቁርኝትና ግንኙነት ማበላሸት አሊያም ማቋረጥ ነው።
- Details
- Written by: Bereket Sulamo
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
በሚበልጥ ክብር መገለጥ
በዘመናችን እየታየ ያለው እንቅስቃሴ በተለይ ከእግዚአብሔር ቃል አኳያ የምናያቸው አብዛኞቹ ነገሮች አሳዛኝ፣ ልብ ሰባ፣ አስከፊ እና ፀያፍ ናቸው። ክርስቲያን እንደ ክርሰቲያንነት የሚታይበት የሌለው፣ እግዚአብሔርን እከተላለሁ የሚል እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የማይሄድ የበዛበት ዘመን፣ ከተግባራዊ ክርስትና ይልቅ አፋዊ ክርስቲያን እና ክርስትና እያየን ያለንበት ዘመን፣ ለአብነት ምስክር መሆን የማንችል፣ ለሌሎች ለሚያምኑም ይሁን ለማያምኑ መልካም ምስክርነት የሌለን ተላላዎች ሆነን እየታየን ነው። ይህ ማንነት ግን ጨርሶ እግዚአብሔራዊ እና ክርስቶሳዊ እና ክርስቲያናዊ አይደለም። ከጥንት የነበሩ በመጽሐፍ ቅዱስ ያየናቸው የእግዚአብሔር ሰዎች በዚህ ማንነት ተገልጠው አናያም፣ ይልቁኑ መንግስታትን በጽድቅ ኖረው፣ አገልግለው ድል ነስተው እግዚአብሔርን አስከብረው አልፈዋል። በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ይሁኑ በእግዚአብሔር ነገር እና ጉዳይ አይደራደሩም፣ እስከመጨረሻው በእግዚአብሔር ጉዳይ ይጋፈጣሉ፣ ይወራረዳሉ በመጨረሻም በእግዚአብሔር ያሸንፋሉ። በሚበልጥ ክብር፣ በሚበልጥ በእግዚአብሔር ኃይልና ክብር መገለጥ በዘመኑ ላይ ባለው ክፋት፣ አመፅ፣ ከእግዚአብሔር በተቃራኒ በቆመ ላይ አይሎ፣ ረግጦ፣ አሸንፎና አጥፍቶ በበላይነት በመቆም የእግዚአብሔርን ስም እንዲገን በማድረግ በገዢነት ለመቆየት ወሳኙ ነው።
- Details
- Written by: Bereket Sulamo
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
አልባሾችህን ጠንቅ ቀህእወቅ
በአገልግሎት ዘመን እጅግ በብዙ ልንጠነቀቅ የሚገባው ነገር ቢኖር በአገልግሎት ዙሪያ አብረውኝ ያሉት እነማን ናቸው፣ አቋማቸውስ እንዴት ነው፣ አብረውኝ መከራ የሚቀበሉ ናቸው ወይስ መከራ አምጪ? በእርግጥ በአገልግሎት ዘመን እጅግ የቅርብ ናቸው የምንላቸው የመከራ አምጪ አሊያም አስመጪ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ አብረኸኝ መከራ ተቀበል ብለን ልንጠራው የማንችል ሊኖር ይችላል፣ አብረኸኝ በጎ ወታደር ሆነህ መከራ ተቀበል የምንለው ላይኖር ይችላል። ብቻ ግን አቅምንና አቋምን ሳያስነኩ መዝለቁ እና የወንጌሉ ሥራ እንዲቀጥል እግዚአብሔር በጎኔ ቆሞ አበረታኝ እንዳለው ጳውሎስ ከሰው በላይ ሊረዳው የሚችል እግዚአብሔር እንዳለ ጠንቅቆ የሚያውቅ ሲሆን፣ የሚረዱት ወንድሞች ባይኖሩትም፣ ለምን መጣህ የልብህን ኩራት እናውቃለን ቢሉት ዳዊት ይህስ ትልቅ ስራ አይደለምን ማለቱ፣ ጎልያድን በተገዳደርከው በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ ማለቱ ረዳቱ እግዚአብሔር እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። ለራእይህ ዘላቂነት፣ ታማኝ ተደርገህ ለተቆጠርክበት አገልግሎትህ መቃናት፣ ለአገልግሎትህ ድጋፍ ሰዎች ወሳኝ መሆናቸው እሙን ነው። ሆኖም ግን አጠገብህ ያሉ ሁሉ ለራእይህ፣ ለመጪው አገልግሎትህ መጥፋት አልያም መሳካት አስተዋጽኦ ሊኖራቸው ይችላል።
- Details
- Written by: Bereket Sulamo
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ

የትውልድ አደራ
የትውልድ ባለአደራነትን መወጣት
አደራ ለአንድ የተወሰነ ተግባር እና ክዋኔ ወይም ግዴታ ለአንድ ሰው ሃላፊነት ወይም ስልጣን መስጠት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት እና በኃላፊነት እንዲወጣ እምነትን መጣል ሲሆን፣ አደራ የአደራን ተግባር በአደራ፣ በመተማመን እና በአደራ የተሰጠው ሰው አቅም ላይ በማመን ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይችላል።
አደራን የመወጣት እና አደራን ከግብ ማድረስ እንዴት ያለ መታደል ነው። በተለይ የትውልድን አደራ ተቀብሎ ትውልድ በመልካም መንገድ የእግዚአብሔርን ሕግ ተከትሎ እንዲሄድ አድርጎ እና በዚህም ፍሬን ማየት እንዴት እጅግ ያስደስታል።
- Details
- Written by: BEREKET SULAMO SUGEBO
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
የተፅእኖ ሰው
እነርሱ በእምነት መንግስታትን ድል ነሡ ጽድቅን አደረጉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ
ዕብራውያን 11፡33
- Details
- Written by: Bereket Sulamo
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ

ያልተጎሰመ አንደበት
“አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ።”— መዝሙር 34፥13።
በአለም ላይ የተደረጉ የትኛውም አይነት ጦርነቶች በቅድሚያ ውጊያን የጀመሩት በዘመናቸው በነበሩት የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም በአንደበት ነው። ክፉ አንደበት የጠብ ጫሪነትን ሚና በከፍተኛ ደረጃ የምትወጣ የክፉ አለም ተምሳሌት ነች። የጦርነት ክተት ይሁን አዋጅ በነጋሪት ጉሰማ ሲታወጅ አንደበት የጦርነትን መጀመር ፋና ወጊና ፈር ቀዳጅ አንደበት ነው። በአንደበት በትንሽ ምላስ የተጫረ የጦርነት ምላጭ ተኩስ የተጀመረው በዚህ በአንደበት አለም ነው።
በክርስትናውም አለም እንዲሁ ያልተጎሰመ አንደበት ሥራው ይኸው ሲሆን በተለይ በወንድማማች መካከል ጠብን በመዝራት የሚታወቀው ይኸው ያልተገራው አንደበት ነው። በተለይ በዚህ ባለንበት ዘመን እጅግ ብዙ አገልጋዮች በድብደባና በዱላ ከመሰበር በላይ በአንደበት የተሰበሩት ኅልቁ መሳፍርት ናቸው።
- Details
- Written by: Bereket Sulamo
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
ሥራ ፈት አንሁን
ሥራ ፈትነት ከምሁራን አንደበት
ሥራ ፈትነትን ከማብራራት አስቀድሜ ነገሬን በዚህ ሥራ በሚለው ጉዳይ ላይ አንድ ምሁር የተናገሩትን ትንሽ ቁም ነገር አዘል ጉዳይ ጠቆም ላድርግና ወደ ተነሳሁበት ሃሳብ ትንሽ ቆየት ብዬ ልመለስ፡፡ ይህ ምሁር ቮልቴር የሚባል ፈረንሳዊ ሊቅና ፈላስፋ ሲሆን ስለ ሥራ የተናገረውን ላንሳ፡- ቮልቴር ሲናገርሥራ ከሶስት ነገሮች የሰውን ልጅ ይጠብቃል ብሎ ይናገራል፡፡
- ከድባቴ ወይም ከድብርት
- ከመጥፎ እኩይ ተጋባርና ድርጊት
- ከድህነት፤ ከችግር ይጠብቃል ይከላከላል በማለት ሙያዊ ምክሩን ይሰጣል፡፡
እውነታው ላይ ተመርኩዘን ስናየውና ስናጤነው ቮልቴር የተናገረው እጅገ እውነት ነው፡፡ በምድራችን አሁን ላይ የምናየው የስራ ፈትነት ካመጣቸው አሉታዊ ችግሮች በይበልጥ ተስተውለው የሚታዩት እነዚህ ናቸው፡፡
ዛሬም በቤተክርስቲያን ውስጥ ከዚህ የተለየ ችግር እያየን አይደለም፡፡ ጉዳዩ የአለማዊ ዕውቀት እና የመንፈሳዊ እውቀት ብለን እንፈርጀው እንጂ በስው ልጅ ላይ እየታየ ያለው ተመሳሳይ ነገር ነው፡፡ ዛሬ ላይ መንግስታትን እያሳሰበ እና እየተፈታተን ያለው ነገር ቢኖር የሥራ ፈት ቁጥር ማሸቀቡና ለዚህም መፍትሄ ማጣቱ ነው፡፡
- Details
- Written by: Mekete Sugebo
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
የእግዚአብሔር ጸጋ
- ሰዎችን ሁሉ የሚያድን ነው።
- ሃጢአተኝነትንና ዓለማዊ ምኞትን የሚያስክድ ነው።
- የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ እንዴት እንደምንጠብቅ የሚያስተምር ነው።
- ራሳችንን መግዛት የሚያስተምር እና የሚያሰለጥን ነው።
- በጽድቅ መኖርን የሚያስተምር ነው።
- እግዚአብሔርን መምሰል የሚያስተምር ነው።
- Details
- Written by: Mekete Sugebo
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
የቀደመው ታሪክና ማንነት የተሻረበት፣ ቀድሞ መታወቂያ የነበረው ማንነት ሙሉ በሙሉ የተወገደበት፣ ማዕረግ ያልነበረን ባለማዕረግ የሆንበት፣ ይህም በአንዱ በክርስቶስ በእግዚአብሔር ልጅ ያገኘነው ልጅነት ነው።