አልባሾችህን ጠንቅ ቀህእወቅ 

በአገልግሎት ዘመን እጅግ በብዙ ልንጠነቀቅ የሚገባው ነገር ቢኖር በአገልግሎት ዙሪያ አብረውኝ ያሉት እነማን ናቸው፣ አቋማቸውስ እንዴት ነው፣ አብረውኝ መከራ የሚቀበሉ ናቸው ወይስ መከራ አምጪ? በእርግጥ በአገልግሎት ዘመን እጅግ የቅርብ ናቸው የምንላቸው የመከራ አምጪ አሊያም አስመጪ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ አብረኸኝ መከራ ተቀበል ብለን ልንጠራው የማንችል ሊኖር ይችላል፣ አብረኸኝ በጎ ወታደር ሆነህ መከራ ተቀበል የምንለው ላይኖር ይችላል። ብቻ ግን አቅምንና አቋምን ሳያስነኩ መዝለቁ እና የወንጌሉ ሥራ እንዲቀጥል እግዚአብሔር በጎኔ ቆሞ አበረታኝ እንዳለው ጳውሎስ ከሰው በላይ ሊረዳው የሚችል እግዚአብሔር እንዳለ ጠንቅቆ የሚያውቅ ሲሆን፣ የሚረዱት ወንድሞች ባይኖሩትም፣ ለምን መጣህ የልብህን ኩራት እናውቃለን ቢሉት ዳዊት ይህስ ትልቅ ስራ አይደለምን ማለቱ፣ ጎልያድን በተገዳደርከው በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ ማለቱ ረዳቱ እግዚአብሔር እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። ለራእይህ ዘላቂነት፣ ታማኝ ተደርገህ ለተቆጠርክበት አገልግሎትህ መቃናት፣ ለአገልግሎትህ ድጋፍ ሰዎች ወሳኝ መሆናቸው እሙን ነው። ሆኖም ግን አጠገብህ ያሉ ሁሉ ለራእይህ፣ ለመጪው አገልግሎትህ መጥፋት አልያም መሳካት አስተዋጽኦ ሊኖራቸው ይችላል።

 1_አብሮ ተልኮ በተቃራኒየሚቆም

ሙሴ የሚወርሷትን ምድር ሊሰልሉ አስራ ሁለቱን ሰላዮች ቢልክም ከቀናት በኋላ የሥራ ግምገማ ምላሽ ከኢያሱና ከካሌብ በተቃራኒ በመቆም የሕዝቡን ልብ ማቅለጣቸው፣ ኢያሱና ካሌብ ግን ልብሳቸውን በመቅደድ ሕዝብን ሊያሳምኑ ታግለዋል። ሰው በመነሻ ሁሉም አንድ ነው፣ በምላሹ ግን ተቃራኒ እና ተፃራሪ ሊሆን ይችላል። አስር ተፃራሪ እንደሚኖር እና እንደማይጠፋ ልናውቅ ይገባል።

 2_የቤትህ ሰው ቤተሰብህ በጠላትነት ይቆማል

ህልም አለህ፣ ራእይ አለህ፣ ዕቅድ አለህ ግን አንድ ነገር ግን አለመርሳት እጅግ ተገቢ ነው። ሁልጊዜ ህልም ያለው በብልጫ መገለጡ አይቀሬ ስለሆነ ሁልጊዜ ዘወትር የህልም ተቃራኒዎች እና ጠላቶች እስከማጥፋት የሚደርሱ ስለሆነ ለህልምህ ዋጋ መክፈል አይቀሬ ነው። ዮሴፍ ከገጠሙት ችግሮች አንደኛው ህልሙ እንዳይሳካ ነው። ወንድሞቹ ያሉት እስኪ ህልሙ እንደሚሳካ እንያለን የሚል ምክርን በጥፋት ገልጠውታል። አስራ አንድ ተፃራሪ እንዳለ ማወቁ ተገቢ ነው። ግን የዮሴፍን ህልም አባቱ ብቻ ይጠብቀው ነበር። ብዙዎች የህልሜ ተጋሪ ነው ብሎ ማሰቡ ተላላነት ነው። ህልምህን የሚጠብቀው አንድ ብቻ ነው። አገልግሎት የአባቴ ልጆች ይደግፉኛል የምትለው አይደለም።

 3_ያመንካቸው ይንሸራተታሉ 

የውስጥ አቅምህ ምን ያህል ወሳኝ እና ሃገራዊ መሆኑን የማያውቁ ሊገፉህ፣ አንተ ውስጥ ያለው ለቅርቦችህ እንኳን እንደሚያስፈልግ ጨርሶ ላያውቁ ይችላሉ። ብዙውን ጊዜ ውስጥህ ያለውን የሚያውቁት የቅርቦች ሳይሆኑ የሩቆች፣ በአጠገብህ ያሉት አይደሉም። ዮፍታሔ ሊያጠፉት የነበራቸው አማራጭ ማንነቱን በሚነካ ንግግር በማጥፋት ነው። ሐሜት ነው? ወሬ ነው? አይቀሬ የክፉዎች የጦር መሳሪያ ናቸው። ወሬ ጥይቱ የማያልቅ ጠብመንጃ ነው። አንደበት፣ ክፉ አለም ጥይቷ የማያልቅ መሳሪያ ነች። ትገፋለህ ነገ ግን መፈለግህ አይቀሬ ነው። የምናምንቴ ልጅ መባል አይቀሬ ነው፣ የልዩ ሴት መባል አይቀሬ ነው። ለወሳኝ ጉዳይ ግን መፈለግ አይቀሬ ነው።

 4_የቅርብህ ያወርዱሃል

ታናሽ ነህ፣ ትንሽ ነህ መባል በእግዚአብሔር ዘንድ ግን የከበረ ነገር አለህ ተብለህ መታሰብህ ሰዎች ላይረዱህ፣ ላይገባቸው፣ ላያውቁት ይችላሉ። ውስጥህን የምታውቀው ግን አንተ እና እግዚአብሔር ብቻ ናችሁ። ታላላቆች ናቸው አዎ ይገፉሃል፣ የማይገፋህ በውስጥህ የራሱን አላማ ያስቀመጠ እግዚአብሔር ብቻ ነው። አንተ ብቻ እግዚአብሔር በውስጥህ ያስቀመጠው ትልቅ ጉዳይ እንደሆነና፣ ለሀገር፣ ለሕዝብ የሚጠቅም መሆኑን መረዳትና ማወቁ ተገቢ ነው። አንተን የማይመጥን ሞራልን የሚነካ ንግግር ሁሉ ሊደርስብህ እንደሚችል ማወቁ ተገቢ ነው።

በመጨረሻም

ለአገልግሎትህ አንዳንድ አልባሾችህን እጅግ ተጠንቀቅ። የማያንቀሳቅስ እና የማያራምድ ነገር ሊያለብሱህ ይችላሉ፣ ሆኖም ግን የራስህን ልምምድ ግን መረዳቱ ተገቢ ነው። ሳኦል ልብሱን ለዳዊት እንካ በዚህ ተዋጋ ማለቱ ያልፈተነውና የማያውቀው እንደሆነ መናገሩ እግዚአብሔር ያስለመደኝ አለ ማለቱ ነው። ያልፈተንከውን፣ ያልለመድከውን ከሚያለብስ፣ ለጊዜው ከሚያለብስህ ሽሽ። ለአገልግሎት ትልቅ ወዳጅ ሊሆን የሚችለው ለአንተም ወዳጅ የራእይህም ወዳጅ የሚሆን ሰው ነው። ዮናታን ለዳዊት ነገ አንተ ንጉስ መሆንህ አይቀርምና ብሎ ማለቱ ለእግዚአብሔርም፣ ለእርሱም፣ ለራእዩም ወዳጅነቱን እያሳየው ነው።

 የማያስኬድህን ከሚያሸክሙ ከሚያለብሱህ መሸሽ 

ብዙውን ጊዜ ፍሬያማ ከማያደርጉን የአንዳንዶች ልማድ ለእኛ የሚበጅና የሚያዋጣን ይመስለንና ተቀብለን በዚህ ልምምድ ልንቀጥል እና ልንሠራ እንጀምራለን። በሌላው ልምምድና ጥሪ አገልግሎት አይቀጥልም። የራስ ልምምድና ጥሪ እሱ ለአገልግሎታችን አዋጪ ነው። የሌላው ልምምድ የራሱ ነው፣ በራስ ጥሪ መቀጠሉ አዋጪ ነው፣ ዘላቂም ነው፣ የአላማና የግብ መጣመር በእርግጠኝነት ይታይበታል። “ዳዊትም ሰይፉን በልብሱ ላይ ታጠቀ፥ ገናም አልፈተነውምና መሄድ ሞከረ። ዳዊትም ሳኦልን፦ አልፈተንሁትምና እንዲህ ብዬ መሄድ አልችልም አለው። ዳዊትም አወለቀ።” — 1ኛ ሳሙኤል 17፥39።

በተለማመድከው ራእይህን አስጀምር አስቀጥል 

በአገልግሎት ዘመን ጅማሮ ከእግዚአብሔር ጋር ለብቻ የነበረ ቀደም ብሎ ያለ ልምምድ እጅግ ወሳኝነት አለው። ይኽም እግዚአብሔር በእኛ ሁኔታ ሊሠራበት የሚወደው ሥራ ነው። አንበሳና ድብ መቆራረጥና መግደል አስለምዶሃል? እሱን ይዘህ ቀጥል። በባዶ እጅ፣ በወንጭፍ አለማምዶሃል? እሱን ይዘህ ቀጥል። “በትሩንም በእጁ ወሰደ፥ ከወንዝም አምስት ድብልብል ድንጋዮችን መረጠ፥ በእረኛ ኮረጆውም በኪሱ ከተታቸው፤ ወንጭፍም በእጁ ነበረ፤ ወደ ፍልስጥኤማዊውም ቀረበ።” — 1ኛ ሳሙኤል 17፥40።

 ከሚደግፉህና ከራእይህ ጎን ከሚቆሙት ጋር ቀጥል

በውስጥህ ያለውን አቀጣጥል፣ በአደራ የተቀበልከውን ቸል አትበል፣ በውስጥ ያለውን እሳት አቀጣጥል ከሚል የተቀበልከውን አደራ ተጠንቀቅለት ከሚልህ ጎን መጣመር እና መጠመድ እሱ አዋጪ ነው። “ዮናታንም የለበሰውን ካባ አውልቆ እርሱንና ልብሱን ሰይፉንም ቀስቱንም መታጠቂያውንም ለዳዊት ሸለመው።” — 1ኛ ሳሙኤል 18፥4።

ወንድም በረከት ሱላሞ ሱጌቦ

+251902910126