ዲዮጥራጢስ


በመልዕክተኛው በዮሐንስ ዘመን በቤተክርስቲያን የነበረ ዋነኛ ሆኖ መታየትን የሚፈልግ፣ የእውነትና የእውቀት ጠላት የሆነ፣ እውነትን ይዘው ለሚጓዙ ዕንቅፋት፣ እውነትን አንግበው ለሚፈጥኑ ትክል ድንጋይ፣ ለቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ግድ የሌለው፣ ዳሩ ግን ዋናቸው ሊሆን የሚወድ የስልጣን ጥመኛ፣ እውነትን አንግበው የሚሄዱትን የማይቀበል፣ የመጣውን በክፉ ቃል በመለፍለፍ የሚነቅፍ (ያልተጎሰመ_አንደበት_አንጋቢ)፣ ለወንድሞች ቦታ የሌለው፣ የማይቀበል፣  ሌሎችን በማሳመፅ እውነትን የያዙትን እንዳይቀበሉ የሚያደርግ፣ ከትዕዛዙ የወጣውን ከቤተክርስቲያን የሚያስወጣ፣ የሚያሸሽ ዛሬም በአጠገባችን፣ በዙሪያችን ያሉ አይደሉምን?

ለጋይዮስ እና ለድሜጥሮስ፦ በመልካም የሚሄዱትን፣ በሁሉ ዘንድ በመልካምነት የሚመሰከርላቸው አጠገብ የማይጠፋ ድዮጥራጢስ፣ ዛሬስ የሉምን? እጅግ በቁጥር በዝተው፣ ከፍታውን ይዘው፣ ከጨለማው አለም ሰራተኞች በላይ ተግተው የሚሠሩ ዛሬም አሉ። ስውር ሥራ፣ ስውር ደባን እንደ አዳኝ አድፍጠው የሚከውኑ፣ ሁሉን ተቆናጥጠው የሚሠሩ ዛሬም አሉ። ርቀው የማይሄዱ የወዳጅ ጠላት እነ አኪጦፌል ዛሬም አሉ። የጥንቱ አኪጦፌል መልኩን ቀይሮ የመጣ ዲዮጥራጢስ እሱ ሳይሆን ይቀር? የድሮ ሰይጣን ዛሬም እሱ ነው። የተሸነፈ ግን ነው!

እነ ዲዮጥራጢስን እንጠንቀቃቸው። ሁሌም አጠገባችን አይታጡም። ትንሿን መልካም ነገር እንዳንሰራ ነገሮችን ያበላሻሉ፣ ያጠፉብናልም።

ይህን ማወቅ እና መረዳት ይሁንልን

ሥራ የሞላበት ትልቅ በር ተከፍቶልኛልና ተቃዋሚዎችም ብዙ ናቸው።”— 1 ቆሮንቶስ 169
በአንድም ነገር እንኳ  በተቃዋሚዎች_አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፥ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤” — ፊልጵስዩስ 128

ዲዮጥራጢስ ድጡ ለአንተ!

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ይሰውረን!

ወንድም በረከት ሱላሞ ሱጌቦ