እስክንድሮሶች
የእውነት እና የሐቅ ተፃራሪዎች፣ በሐሳብ ሙግት ሳይሆን የሚጠሉትን በያዙት አቋምና እምነት የማይሟገቱ፣ ይልቁኑ በተቃውሞና በማጥላላት ላይ ተጠንዘው የሚገኙ፣ እውነትን እድሜ ሚያሳጥሩ የመሰላቸው፣ የሚቃወሙትን ግን እያጠነከሩት እንደሆነ የማይገባቸው፣ የራሳቸውን በአግባቡ ሳያውቁ የሌላውን እውነት ለማደብዘዝ፣ አዚም የሚያደርግ ባልጠፋበት #የዘመኑ_አዚመኞች፣ ግን ሳያውቁት ሌላውን እያጠነከሩ ያሉ #የዘመኑ_አስክንድሮሶች መኖራቸውን ለቅፅበት መዘንጋት የለብንም። ከሚቃወሙ የሚያነጥሩት ነሐስ አዋጪ መሆኑን ቢረዱ ምን ያህል መልካም ነበር? ምን ያህል ትርፋማ ይሆኑ ነበር። በተለይ የወንጌልን እውነት ይዘው እና አንግበው የሚንቀሳቀሱትን፣ በዘመኑ ላይ እየሆነ ያለውን ኢ-መፅሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሮቶችን ነቅሰው በማውጣት እውነታውን ፍንትው አድርገው ገልጠው እና ገልጸው የሚያስተምሩትን በትችት ናዳ ለማሸማቀቅ የሚታትሩ #የዘመኑ_አዚሞች_አዚመኞች እነ #እስክንድሮስ እንዳሉ መረዳቱ እጅግ ጠቃሚ ነው።
“የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ እጅግ ከፋብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይመልስለታል።” — 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥14።
የእግዚአብሔርን እውነት ይዘው እውነት እንድትታይ ሌት ተቀን ለምትታትሩ የእውነት ታጋዮች የሙግት ጊዜ ባይኖረን ግን እውነትን በፍቅር በመያዝ እና እየገለጥን መኖሩ ተገቢ ቢሆንም #ከእስክድሮስ መጠበቁ ግን እጅግ ጠቃሚ ነው። #እስክንድሮስ ከተቃውሞ ውጭ እንደማይሆን ማወቁም ተገቢ ነው። “አንተም ደግሞ ከእርሱ ተጠበቅ፥ የምንናገረውን እጅግ ተቃውሞአልና።”— 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥15።
#የእነ_እስክድሮስ አቅማቸውም አቋማቸውም ተቃውሞ መሆኑ ሳይዘነጋ የተሰጠንን ሥራችንን እየሠራን መቀጠሉ እርሱ ዋናው ነገር ሲሆን ቦታም አለመስጠቱ እጅግ ተገቢ ነው። #እስክንድሮስ ጊዜን አባካኝ መሆኑን አለመርሳቱ ተገቢ ነው። ክርክር ጊዜና ዕድል መስጠት መሆኑን ለአፍታ_ለቅፅበት መዘንጋት የለብንም። ሥራው የተማርነውን እና የምናስተምረውን ትምህርት እግር በእግር የሚቃወም መሆኑን መዘንጋት የለብንም።
“ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት የሚቃወሙትን መለያየትንና ማሰናከያን የሚያደርጉትን ሰዎች እንድትመለከቱ እለምናችኋለሁ፥ ከእነርሱ ዘንድ ፈቀቅ በሉ፤” — ሮሜ 16፥17።
#እነ_እስክንሮስ በክርስቶስ ትምህርት የማይኖሩ አምላክ የሌላቸው መሆኑን ማወቁ ተገቢ ነው፣ ተቃውሞአቸውም ይህ ነው። በክርስቶስ ትምህርት ኖረው አምላክ ያላቸውን በማሳት የተካኑ መሆናቸውን ማወቁ ተገቢ እና ወሳኝ ነገር ነው።
መፍትሄው
1- መጠበቅ
2- ፈቀቅ ማለቱ ተገቢ ነው።
ሰናይ አገልግሎት እና ዘመን ይሁንልን!
ወንድም በረከት ሱላሞ ሱጌቦ