The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
- Details
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
የዮሐንስ ወንጌል 17፥17 በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው።
እግዚአብሔር የሚቀድሰን ወይም የሚለየን በቃሉ እውነት ነው። የእግዚአብሔር ቃል እውነት በሰው ልብ ውስጥ ሲያድር የመለየትና የመቀደስ ብቃት አለው።
- Details
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
ማቴ. 1፡18 የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። 19 እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ። 20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ። 21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።
- Details
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
የሰው ማንነቱ በምልልሱ ይታወቃል። የምንመላለስበት አካሄድ ደግሞ የመሆናችንና የሆነውን የመረዳታችን ውጤት ነው። ወደ ፊልሞና
1፥6 "የእምነትህም ኅብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ፤" ወደ ኤፌሶን ሰዎች
1፥17 "የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።"
- Details
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
በጌታ ደስ ይበላችሁ ሲል ለምን እንዳለ ማወቁ በጣም ይረዳናል። ሰዎች የሚደሰቱት "ይህ አለን" ብለውና ይህን ያላቸውን ነገር በማሰብና በማሰላሰል ነው። ነቢዩ እንባቆምን በጽሑፉ ስናየው በህይወቱ ሲያስደስቱት የነበሩ ነገሮች ነበሩ። እነዚህ የሚያስደስቱት ነገሮች ከህይወቱ በጎደሉ ጊዜ የሚደሰትበትን ነገር ሲያስብ ጎድሎበት አየ። በዚህ ጊዜ ነው አንድ ከሁሉ በላይ ሊታሰብ የሚገባውን ነገር የተረዳው፤ ይኸውም እግዚአብሔር። ይህ እግዚአብሔር ወገኑ መሆኑን ሲረዳና ሲያስብ ደስታውም ደስታውም በእርሱ መሆኑን ተረዳው። ይህ እግዚአብሔር ለእንባቆም የመድኃኒቱ አምላክ ነበር።
- Details
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
መጽሐፈ ምሳሌ 18፥10 የእግዚአብሔር ስም የጸና ግምብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል።
የእግዚአብሔር ስም ለሚታመኑት በከፍታ እንደተሰራ የመጠከለያ ግንብ ነው። ጠላት ያለውን ሁሉ ቢወረውር በዚህ ስም የተከለለውን ሊነካው አይችልም። ስሙ የጸና ግምብ ነው።
በከፍታ ስፍራ እንደተቀመጠ ሰው በዚህ ስም የተደገፈ ሁሉ እንደዚሁ በከፍታ ስፍራ ሆኖ ይጠበቃል። የጻድቅም ተስፋው የእግዚአብሔር ስም ነው። ጻድቅ ሁልጊዜ የሚሮጠው ወደዚህ ስም ነው።
- Details
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
የያዕቆብ መልእክት1፥17 በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።
እግዚአብሔር የበጎ ስጦታ ሁሉ ደግሞም የፍጹም በረከት ሁሉ መገኛ ነው። የሚሰጠውም ከማንነቱ የተነሳ ነው፤ ይህም ማንነቱ ፍቅር ነው። ይህ ፍቅር የሆነው አምላክ በሚለዋወጥ ነገር የማይለዋወጥ፤ በሚቀያየርም ሁነት የማይቀያየር ፍጹም የሆነ አምላክ ነው።
የእግዚአብሔር ስጦታ በጎ ነው፤ እግዚአብሔር ክፉን አይሰጥም፤ ከእርሱ ዘንድ ክፉ አይወርድም። ነገር ግን በጎ የሆነው አምላክ ለሰው ልጆች ሁሉ በጎን ነገር ማድረግ ይወዳል። ስለዚህም የበጎነት መገለጫው የሆነውን ልጁን ሰጥቶናል። ስለዚህም የእርሱን በጎነት እናወራለት ዘንድ በልጁ በኩል ልጆቹ አድርጎ ባርኮናል። እግዚአብሔር የሰጠው ትልቁ የበጎነቱ ስጦታ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ እርሱንም በማመን ያገኘነው ልጅነት የእግዚአብሔር በጎነት ነው። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2፥9
እግዚአብሔር የባረከንም በረከታችን ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በእርሱ ሆነን በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ ተባርከናል። ይህም በረከታችን እንከን የማይወጣለት፣ የማይጨመርበት ፍጹም የሆነ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ሳይሰስት፣ ሳያስለምን፣ ሳያጎድል የባረከን እግዚአብሔር ይባረክ።
- Details
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ የእርሱን ህይወት ተካፋዮች እንዲሆኑ ጠርቷቸዋል። ይህም ጥሪ በወንጌል እውነት በኩል የሚሆን የመዳንና ህይወትን የመካፈል ጥሪ ነው።
ወደ ዕብራውያን 3፥1 ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ
- Details
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
ክርስቶስ የመጣው ሊያሳርፈን ነው። እኛ ልንፈጽመው ያልቻልነውን የጽድቅን ሥራ እርሱ ፈጽሞልን በእኛ ላይ የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደምስሶታል። ይህም የዕዳ ጽሕፈት ይቃወመን እና ይከሰን የነበረ ትእዛዝ ሲሆን ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀሉ ስራ ከመንገዳችን ላይ አንስቶታል። ስለዚህም ዳግመኛ በዚህ ትእዛዝ ላንያዝ ዘንድ ነጻ ወጥተናል። ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ተሰቅሎ፣ ሞቶ፣ ተቀብሮ ደግሞም ከሙታን ተነስቶ ወደ ነጻነታችን አስገብቶናል። እንኳን በክርስቶስ ኢየሱስ ወደዚህ የእረፍት ነጻነት መጡ። ክብር ለስሙ ይሁን።
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2፡14 በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤
- Details
- Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
የእግዚአብሔር ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ ስለፈሰሰልን ሰዎችን ሁሉ መውደድ ሆኖልናል። ፍቅርን የምንፈጥረው ሳይሆን የምንቀበለው እንደሆነ በዚህ እናያለን። ይህም ፍቅር ደግሞ የእግዚአብሔርን ባህርይ ያሳየናል።