የእግዚአብሔር ሞገስ

ሞገስ

ሞገስ ማለት ምን ማለት ነው? “ሞገስየሚለው ቃልካሪስከሚለው ከግሪክ ቃል የተወሰደ እና የተዛመደ፣ አቻ ትርጉም ያለው ሲሆን የእግዚአብሔር ባለጠግነት ምህረት ነፃ ስጦታ ሽልማት ያልተገባ ወይም ለማይገባው፣ ሊገባውም ለማይችል ግን የተሰጠ፣ የተቸረ የሚልን ትርጉም ይይዛል፣ ይዟልም፡፡ 

 

ብዙውን እኛ ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር እንዲሰጠን ከምንፈልጋቸው ነገሮች አንዱ ሞገስ ነው። በእርግጥ እግዚአብሔር ቸር ነው፣ ለጋሽም ነው፣ ሰጪም ነው። ሆኖም ግን በመሠረታዊነት የምንስታቸው ወሳኝ ነገሮች፣ ከግንዛቤ የማናስገባቸው፣ ችላም የምንላቸው ናቸው። ግን እጅ ወሳኝ የሆኑ መሠረታዊ ነገሮች እና እውነታዎች ናቸው። እነዚህም መሠረታዊ ነገሮች ከእግዚአብሔር የምንፈልገውን ነገር የሚያሰጡን ናቸው። ቅድመ ሁኔታን አመላካች ናቸው። ስለዚህ አውቀን፣ ተረድተን ልናደርጋቸው፣ ልንተገብራቸው የግድ የሆኑ እና በቅድመ ሁኔታ ከእኛ የሚጠበቁ ናቸው። የሚጠበቅብንን ካደረግን በቀጣይ ከእግዚአብሔር የለመንነውንና የምንጠብቀውን ለመቀበል የምንችልበት ነው።

 

ከእግዚአብሔር ቃል ስለ ሞገስ በጥልቀት አብዝተን ባወቅን ጊዜ አስገራሚ ነገሮች በህይወታችን ላይ ተችረን እናገኛለን፡፡ከነዚህም አንዱን "ሞገስ" በሚለው ላይ በመሠረታዊነት እንማር። ከእኛ ከክርስቲያኖች ከሚጠበቁ አቢይና ወሳኝ ነገሮች መካከል በምሳሌ መጽሐፍ 3፡3-4 ያሉትን የእግዚአብሔር ቃል እናጢን፡፡

 

ከእኛ ከሚጠበቁ አቢይ ጉዳዮች

1. ምህረት

2. እውነት

3. ምህረትና እውነት ከእኛ መራቅ የለባቸውም

4. ምህረትና እውነት በአንገታችን ይታሰራሉ

5. ምህረትና እውነት በልባችን ጽላት ይጻፋሉ

አነዚህን እውነታዎች በቅድመ ሁኔታ በእኛ ዘንድ አለመኖራቸው እና አለመተግበራቸው  ለምንፈልገው "ሞገስ" እየተቸገርን እንደሆነ በውል አናውቅም።

 

ብዙውን ጊዜ እኛ ክርስቲያኖች በመርህ ላይ ክርስትናችን መመስረቱን ጨርሶ አንገነዘብም፣ አንረዳም። ለምንፈልገው የትኛውም ጉዳይ ቀዳሚው ከእኛ ዘንድ እንዳለና የሚጠበቅብንም እንደሆነ በመሠረታዊነት አናውቀውም። ከእግዚአብሔር መፈለግን እንጂ እግዚአብሔር ከእኛ በቀዳሚነት የሚፈልገው እንዳለ አናውቅም። ለዚህ ነው ሰለሞን ጠንቅቆ በመረዳቱ "የሞገስን" አስፈላጊነት በመረዳቱ፣ መችና እንዴት ምን ብናደርግ እንደምናገኝ አበክሮ ሚያስተምረን።

1.   የምህረት ልብ የለንም፣ ለሌሎች ምህረትን አናደርግም ከዚህ የተነሳ ከእግዚአብሔር የምንፈልገውን "ሞገስን" አናገኝም።

2.   እውነት በእኛ ዘንድ የለም። ብዙውን ጊዜ ነገሮቻችን በእውነትና ከእውነት ጋር የተዋዛ አይደለም፣ ከእውነት በራቀ አይነት እንቅስቃሴ ላይ ዘወትር እንገኛለን።

3.   እግዚአብሔር ከሚፈልጋቸው ነገሮች ርቀን፣ በተለይም ማንነታችን ሙሉ በሙሉ ከእግዚአብሔር ፍላጎት እጅግ ርቀን መኖራችን "ሞገስን" አጥተን፣ በሌሎችም ዘንድ ቅቡልነትን አጥተናል።

 

³ ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው። በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ። ምሳሌ 3:3-4

 

ሞገስ ቤትና በማን ፊት የሚገኝ ነው

  1. በእግዚአብሔር ፊት የምናገኘው ነው፡- ³ ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው። በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ። ምሳሌ 3:3-4የእግዚአብሔር ሞገስ በተለይ በጌታችን በኢየሱስ ያመነ እና የዳነ ከእግዚአብሔር ሞገስን ያገኛል፡፡
  2. በሰው ፊት የምናገኘው ነው፡- ³ ምሕረትና እውነት ከአንተ አይራቁ፤ በአንገትህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው። በእግዚአብሔርና በሰው ፊትም ሞገስንና መልካም ዝናን ታገኛለህ። ምሳሌ 3:3-4 በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት፡- እኔንስ ለመቀበል በምን ነገር በፊትህ ሞገስ አገኘሁ? እኔ እንግዳ አይደለሁምን? አለችው፡፡ ቦዔዝም፡- ባልሽ ከሞተ በኋላ አባትሽንና እናትሽን የተወለድሽባትንም ምድር ትተሽ ቀድሞ ወደ ማታውቂው ሕዝብ እንደመጣሽ ለአማትሽ ያደረግሽውን ነገር ሁሉ ፈጽሞ ሰምቻለሁ፡፡ እግዚአብሔር እንደስራሽ ይስጥሽ ከክንፉም በታች መጠጊያ እንድታገኚ በመጣሽበት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ደመወዝሽ ፍጹም ይሁን አላት፡፡ ሩት 2፡1-14፡፡ በየቀኑም በአንድ ልብ ሆነው በመቅደስ እየተጉ በቤታቸውም እንጀራ እየቆረሱ በደስታና በጥሩ ልብ ምግባቸውን ይመገቡ ነበር እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በሕዝብ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው፡፡ ጌታማ የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር፡፡ የሓዋሪያት ሥራ 2፡46-47፡፡

 

የሞገስ አይነቶች

  1. የተቀባይነት ሞገስ፡- ከስነ ልቦና ጫና እና ከስደተኝነት ስሜት የሚያወጣ ሞገስ

ይህ የተቀባይነት ሞገስ እግዚአብሔር በባዕድ አገር ሰው እንዳይገፋቸው፣ እንዳይነካቸው  ለህዝቡ እግዚአብሔር በገዙአቸው ዘንድ እግዚአብሔር "ሞገስን" ሰጣቸው። በእርግጥ እግዚአብሔር ለቃል ኪዳን ሕዝቡ ከብደው እንዲገኙ "ሞገስን" ሰጥቶአቸዋል። በእርግጥ እግዚአብሔር ለአብርሃም በገባው ቃል መሠረት እግዚአብሔር ሕዝቡን "በሞገስ" ባርኳቸዋል፣ ተቀባይነትም አግኝተዋል።እግዚአብሔርም በግብፃውያን ፊት ለሕዝቡ ሞገስን ሰጠው። ሙሴም በፈርዖን ባሪያዎችና በሕዝቡ ፊት በግብፅ አገር እጅግ የከበረ ሰው ነበረ።” — ዘጸአት 113፡፡ በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት፡- እኔንስ ለመቀበል በምን ነገር በፊትህ ሞገስ አገኘሁ? እኔ እንግዳ አይደለሁምን? አለችው፡፡ ቦዔዝም፡- ባልሽ ከሞተ በኋላ አባትሽንና እናትሽን የተወለድሽባትንም ምድር ትተሽ ቀድሞ ወደ ማታውቂው ሕዝብ እንደመጣሽ ለአማትሽ ያደረግሽውን ነገር ሁሉ ፈጽሞ ሰምቻለሁ፡፡ እግዚአብሔር እንደስራሽ ይስጥሽ ከክንፉም በታች መጠጊያ እንድታገኚ በመጣሽበት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ደመወዝሽ ፍጹም ይሁን አላት፡፡ ሩት 2፡1-14፡፡ ሩት የትውልድ አገሯ ባልሆነ አገር ከስጋዋ ዘር ባልሆነው ትውልድ ውስጥ የተቀላቀለችው እንዲሁም ለኑሮዋ የሚያስፈልጋትን ቃርሚያ የተቀበለችው እግዚአብሔር በቦኤዝ ፊት በሰጣት ሞገስ ብቻ ነው፡፡

 

አስቴር በሐማ ምክንያት በአይሁድ ላይ በታወጀው ሞትና ጥፋት ከንጉስ አርጤክስስ ዘንድ በምትቀበለው ንግስና መካከል ባለመናወጥ ጸንቶ በመቆም ነገሮች እንዲገለበጡ ያደረገችው ወደ እግዚአብሔር በመፀለያቸው በንጉሱ ፊት እግዚአብሔር በሰጣት ሞገስ ነው፡፡ ንጉሱም ንግስቲቱ አስቴር በወለሉ ላይ ቆማ ባየ ጊዜ በአይኑ ሞገስ አገኘች ንጉሱም በእጁ የነበረውን የወረቁን ዘንግ ለአስቴር ዘረጋላት አስቴርም ቀርባ የዘንጉን ጫፍ ነካች፡፡ አስቴር 5፡2፡፡ ወገናቸው ያልሆኑ በምረኮ የያዙአቸው ታዝዘው እሺ እንዲሉ የሚያሰኝ ፈቃደኛም እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ እስራኤላውያን ግብፃውያንን የወርቅ ዕቃ እነዲሰጡአቸው እንዲጠይቋቸው ነገረው፡፡ ዘፀአት 3፡21-22፡፡ እግዚአብሔር እስራኤላውያን የጠየቁትን መቀበል የሚያስችላቸውን ሞገስ ስለሰጣቸው እንደ ተነገራቸው ወረቁንና ብሩን በዝብዘው ከግብፅ ወጡ፡፡ ዘፀአት 12፡36፡፡

 

2. የመታየት ሞገስ፡- የበላይነት የሚገለጥበት

በተለይ ከእግዚአብሔር ባህሪ ልንገረምበት የሚገባው እግዚአብሔር ህዝቡን በባዕድ ሃገር ላይ እንዴት አድርጎ "በሞገስ" መባረኩ ነው። በበላይነት ኖረው እግዚአብሔርን በባዕድ አገር አስከብረው እና አሳይተው  የሚወጡት እግዚአብሔር በሰጣቸው "ሞገስ" ነው። ይህ "ሞገስ" የተደበቁት እንዲታዩ የሚያደርግ፣ ከተደበቁበት እንዲወጡ የሚያደርግ፣ በልዩነት የሚያኖር፣ ቦታን የሚያስለቅቅ እና አስለቅቆ ቦታን፣ ስልጣንን፣ ሹመትን የሚያሰጥ ነው።ወደ ንጉሡም ትገባ ዘንድ የመርዶክዮስ አጎት የአቢካኢል ልጅ የአስቴር ተራ በደረሰ ጊዜ የሴቶች ጠባቂው የንጉሡ ጃንደረባ ሄጌ ከሚለው በቀር ምንም አልፈለገችም ነበር፤ አስቴርም በሚያዩአት ሁሉ ዓይን ሞገስ አግኝታ ነበርና።”— አስቴር 215፡፡ ቦዔዝ በእርሱ እርሻ ላይ ከሎሌዎች በስተኋላ በምትቃርምበት ጊዜ ሎሌዎቹን ይህች ማን ናት ብሎ በመጠየቅ ባገኘው ምላሽ ቃርሚያ ተዉላት አለ፡፡ በሞገስ በመታየቷ ያገኘችው በረከት፡፡ በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት፡- እኔንስ ለመቀበል በምን ነገር በፊትህ ሞገስ አገኘሁ? እኔ እንግዳ አይደለሁምን? አለችው፡፡ ቦዔዝም፡- ባልሽ ከሞተ በኋላ አባትሽንና እናትሽን የተወለድሽባትንም ምድር ትተሽ ቀድሞ ወደ ማታውቂው ሕዝብ እንደመጣሽ ለአማትሽ ያደረግሽውን ነገር ሁሉ ፈጽሞ ሰምቻለሁ፡፡ እግዚአብሔር እንደስራሽ ይስጥሽ ከክንፉም በታች መጠጊያ እንድታገኚ በመጣሽበት በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ዘንድ ደመወዝሽ ፍጹም ይሁን አላት፡፡ ሩት 2፡1-14፡፡

 

3. የመብለጥ ሞገስ፡- የበላይነት የሚገለጥበት

ከእኛ በሚጠበቀው ራስን መጠበቅ ሲሆን፣ ከማይመች ነገር መራቃችን፣ ራሳችን በጠበቅን ጊዜ በተለይ በጸሎት ላይ ያለን አመለካከት ያልተንጋደደ ከሆነ በማንም ዘንድ ልቆ መታየት አይቀሬ ነው።ንጉሡም ከሴቶች ሁሉ ይልቅ አስቴርን ወደደ፥ በዓይኑም ከደናግል ሁሉ ይልቅ ሞገስንና መወደድን አገኘች፤ የመንግሥቱንም ዘውድ በራስዋ ላይ አደረገ፥ በአስጢንም ፋንታ አነገሣት።”— አስቴር 217 የእግዚአብሔርን መንፈስ ተቀበልን ማለት ከመንፈሱ ጋር አብሮ የምናገኘው አንዱ ታላቅ እና ወሳኝ ነገር ሞገስ ነው፡፡ ይህንንም ነው ዳንኤል በግዞት አገር የተቸረው፡፡ ዳንኤልም መልካም መንፈስ ስላለው ከአለቆችና ከመሳፍንት በለጠ ንጉሱም በመንግስቱ ሁሉ ላይ ይሾመው ዘንደ አሰበ፡፡ ትንቢተ ዳንኤል 6፡3፡፡

 

4. የመወደድ ሞገስ፡-የጥላቻ፤ የስነልቦና ጫና፤ የባይተዋርነት መንፈስ የሚመታበት

ከእኛ በሚጠበቀው ራስን መጠበቅ ሲሆን፣ ከማይመች ነገር መራቃችን፣ ራሳችን በጠበቅን ጊዜ በተለይ በጸሎት ላይ ያለን አመለካከት ያልተንጋደደ ከሆነ በማንም ዘንድ ልቆ መታየት አይቀሬ ነው።ንጉሡም ከሴቶች ሁሉ ይልቅ አስቴርን ወደደ፥ በዓይኑም ከደናግል ሁሉ ይልቅ ሞገስንና መወደድን አገኘች፤ የመንግሥቱንም ዘውድ በራስዋ ላይ አደረገ፥ በአስጢንም ፋንታ አነገሣት።”— አስቴር 217

 

እግዚአብሔርም በጃንደረቦቹ አለቃ ፊት ለዳንኤል ሞገስንና ምሕረትን ሰጠው።” — ዳን8ኤል 19

 

5. የማስለቀቅ፣ የመበዝበዝ ሞገስ፡- በለፉበትምድር ምንዳው በባዶ እጅ አለመመለስ፤ የልፋትን ማግኘት

እስራኤላውያን የአራት መቶ ሠላሳ አመትን የባርነትን ጊዜ አብቅቶ የኤርትራን ባህር ተሻግረው ከመምጣታቸው በፊት ባዶ እጃቸውን እንዳይወጡና ጉዞአቸውንም እንዳይጀምሩ በመበዝበዝ ወጡ። ይህ ሞገስ ከማስደንገጥ ጋር ያለ "ሞገስ" ነው።እግዚአብሔርም ለሕዝቡ በግብፃውያን ፊት የፈለጉትን እንዲሰጡአቸው ሞገስን ሰጠ። እነርሱም ግብፃውያንን በዘበዙ።” — ዘጸአት 1236

 

በግብፃውያንም ፊት ለዚህ ሕዝብ ሞገስን እሰጣለሁ፤ እንዲህም ይሆናል፤ በሄዳችሁ ጊዜ ባዶ እጃችሁን አትሄዱም፤”— ዘጸአት 321

 

6. የመታወቂያ ሞገስ፡- በስም እስከመጠራት ያደርሳል

በእግዚአብሔር ዘንድ በእርግጥም መታወቃችን አንዱ መለያ "ሞገስ" ነው። "ሞገስን" ያገኘ በእግዚአብሔር ዘንድ መታወቁ ነው ማለት ነው። የታወቀ ከእግዚአብሔር አንዳች የሚያጣው ነገር የለም። ልመናውን ያገኛል።እግዚአብሔርም ሙሴን፦ በፊቴ ሞገስ ስላገኘህ በስምህም ስላወቅሁህ ይህን ያልኸውን ነገር አደርጋለሁ አለው።” — ዘጸአት 3317

 

 7. ከፍታን የሚያስረግጥ ሞገስ፡-ታች ከተገኘንበት በሹመት ከባለስልጣናት ጋር መቀመጥ

ራስን ከአለማዊ አመለካከትና ከኃጢአተኛ ከሚመጣ ግብዣ ራስን በመጠበቅ እና በመሸሽ የሚገኝ "ሞገስ" ነው።ዮሴፍም በጌታው ፊት ሞገስን አገኘ፥ እርሱንም ያገለግለው ነበር፤ በቤቱም ላይ ሾመው፥ ያለውንም ሁሉ በእጁ ሰጠው።” — ዘፍጥረት 394

 

እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ፤ ምሕረትንም አበዛለት፥ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሰጠው።

  ዘፍጥረት 3921

 

8. የበረከት፣ የመውረስ ሞገስ፡-የተትረፈረፈ ህየወት

ስለ ንፍታሌምም እንዲህ አለ፦ ንፍታሌም በሞገስ ጠግቦአል፥ የእግዚአብሔርንም በረከት ተሞልቶአል፤ ባሕሩንና ደቡቡን ይወርሳል።” — ዘዳግም 3323

 

ለማን ይሰጣል?

1- የሚጸልዩ ያገኛሉ

ብዙውን ጊዜ ጸሎትን የመርሃ ግብር ማሟያ አድርገን የምንከውነው ሥራ አድርገን፣ እውነታው ላይ ሳይሆን በቃ ግዴታ አድርገን ምን እባላለሁ በሚል እሳቤ የምናደርገው ነው። ጸሎት ግን እግዚአብሔርን የምናመልክበት፣ የምንነጋገርበት፣ ብዙ ከእግዚአብሔር የምንሰማበት ነው። "ለሞገስ" መሠረታዊው ነገር በእጅጉ ወሳኙ ጸሎት ነው።ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፥ እርሱም ሞገስን ይሰጠዋል ፊቱንም በደስታ ያሳየዋል፤ ለሰውም ጽድቁን ይመልስለታል።” — ኢዮብ 3326

 

2-ለትሁታን ይሰጣል

በተለይ እኛ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ብዙውን ጊዜ ስተን የምንገኝበት መሠረታዊ ነገር ትህትና ነው። በተለይ ትሁት የሆነ ሰው እንደ ሞኝ የሚቆጠር፣ እንደ አላዋቂ የሚቆጠር ተደርጎ ይቆጠራል። እንደነዚህ ያሉ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን የሚያገኙና የሚሰጣቸው ነው። ስለዚህ ትሕትና ላይ መሥራት፣ መትጋት አለብን።  እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ።” — ሮሜ 1216 ስለዚህ የትህትና የመጨረሻው ዋጋ ከእግዚአብሔር ሞገስን መቀበል ነው።በፌዘኞች እርሱ ያፌዛል፥ ለትሑታን ግን ሞገስን ይሰጣል።” — ምሳሌ 334

 

3- እግዚአብሔርን ያገኘ

እግዚአብሔር ሁልጊዜ የእርሱን ፊት እንድንፈልግ ይሻል። እግዚአብሔር ፊቱን እንድንሻ ይፈልጋል። እንደ ትዕዛዝም የተሰጠን እንደሆነ እየተረዳን አይደለም።አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።” — መዝሙር 278 ስለዚህ ሁልጊዜ የሚገኘውን እግዚአብሔርን መፈለግ ይገባናል።እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤”— ኢሳይያስ 556 ስለዚህ እሱን እግዚአብሔርን ስናገኘው "ሞገስ" ይሰጠናል።

እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና፥ ከእግዚአብሔርም ሞገስን ያገኛልና።” — ምሳሌ 835

 

4-ደኅና ሰው

ከክፋት ያልጸዳ ልብ፣ አስተሳሰብ፣ አእምሮ፣ ነፍስ ከእግዚአብሔር አንዳች የሚቀበሉ አይደሉም። ከረከሰ ማንነት ጋር እግዚአብሔር በምንም ተአምር ህብረት  የለውም። ብዙውን ጊዜ ለምን "ሞገስ" እንዳጣን ሰከን ብለን አለማሰቡ፣ ምክንያቱ ምንድነው ብሎ ራስን አለመመርመር ትልቁ በሽታችን ነው። ስለዚህ "ሞገስን" ለማግኘት ምን እናድርግ? ክፋትን አርቀን መልካም ሰው፣ ደኅና ሰው እንሁን።አሁን ግን እናንተ ደግሞ ቍጣንና ንዴትን ክፋትንም፥ ከአፋችሁም ስድብን የሚያሳፍርንም ንግግር እነዚህን ሁሉ አስወግዱ፤”— ቆላስይስ 38 ስለዚህ "ሞገስን" የሚያገኙ ከክፋት የራቁ፣ ደኅና ሰዎች ብቻ ናቸው። ስለዚህ ደህና እንሁን።ደኅና ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን ያገኛል፤ ተንኰለኛውን ሰው ግን ይቀሥፈዋል።”— ምሳሌ 122

 

ሞገስ በክርስቲያን ሕይወት ሲገለጥ ምን ይሆናል

1.   የሚሰራው ስራ ይከናወንለታል

ቤቀኑም በአንድ ልብ ሆነው በመቅደስ እየተጉ በቤታቸውም እንጀራ እየቆረሱ በደስታና በጥሩ ልብ ምግባቸውን ይመገቡ ነበር እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በሕዝብ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው፡፡ ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር፡፡ የሐዋሪያት ሥራ 2፡46-47፡፡

2.  መፈራት ይሆናል

የቀደሙ የእምንት አባቶች በዘመናቸው የገጠሙአቸውን ተግዳሮቶች ድል ያደረጉት እምነታቸው እንዳለ ሆኖ አንደኛው ሞገስ ነበር፡፡ በዚህ ሞገስ አሰፈርተው እና አሸንፈው እግዚአብሔርን አስከብረውበታል፡፡ሐዋሪያትም ለወንጌል ሥራ በአገራትና በሕዝብ ዘንድ መፈራትንና ከብዶ መታየትን የሰጣቸው የእግዚአብሔር ሞገስ ነው፡፡ በብዙ ሌላ ቃልም መሰከረና ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ ብሎ መከራቸው፡፡ ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ በዚያም ቀን ሶሰት ሺህ የሚያህል ነፍስ  ተጨመሩ በሓዋሪያትም ትምህርና በኅብረት እንጀራውንም በመቁረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር፡፡ ነገር ግን በየሰው ሁሉ ፍርሃት ሆነ በሐዋሪያትም እጅ ብዙ ድንቅና ምልክት ተደረገ፡፡ ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ ያለቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ፡፡ መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉት ነበር፡፡ በየቀኑም በአንደ ልብ ሆነው በመቅደስ እየተጉ በቤታቸውም እንጀራ እየቆረሱ በደስታና በጥሩ ልብ ምግባቸውን ይመገቡ ነበር እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ በሕዝ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው፡፡ ጌታም የሚድኑትን ዕለት ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር፡፡ የሐዋሪያት ሥራ 2፡46-47፡፡

 

ለምን ሰጠን

እግዚአብሔር አምላክ ምሕረትንና እውነትን ስለ ወደደ፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም። መዝሙር 8411

 

በምርኮ አገር

በምርኮ አገር እግዚአብሔር በዘመናቸው በሕይወታቸው ላይ በባዕድ አገር እግዚአብሔር በሰጣቸው ሞግስ የሆነላቸውን ጥቂቶችን የእምንት አርበኞችን ከእግዚአብሔር ቃል እንመልከት

በማረኩአቸውም ሁሉ ፊት ሞገስን ሰጣቸው።” — መዝሙር 10646

 

አገራቸው ባልሆነ፣ የዜግነት ምድራቸው ባልሆነበት፣ የተወለዱበት ምድር ያልሆነ፣ የቃል ኪዳናቸው አገር ያልሆነበት ግን በዚህ "ሞገስ" እግዚአብሔር በሰጣቸው የበላይ፣ ገዢ ሆነው፣ ተቆጣጥረው ኖረዋል፣ እግዚአብሔርንም አስጠርተዋል፣ አሰከብረዋል።

 

1.  ዮሴፍ- በወንድሞቹ የተሸጠ

እግዚአብሔርም ከዮሴፍ ጋር ነበረ፤ ምሕረትንም አበዛለት፥ በግዞት ቤቱም አለቃ ፊት ሞገስን ሰጠው።” — ዘፍጥረት 3921 ከመከራውም ሁሉ አወጣው በግብፅም ንጉስ በፈርዖንም ፊት ሞገስንና ጥበብን ሰጠው በግብፅና በቤቱ ሁሉ ላይም ቢትወደድ አድርጎ ሾመው፡፡ የሐዋሪያት ሥራ 7፡10፡፡

 

2.  አስቴር- በምርኮ በግዞት በቤተ መንግስት ለንጉስ ተመርጣ የሔደች

ወደ ንጉሡም ትገባ ዘንድ የመርዶክዮስ አጎት የአቢካኢል ልጅ የአስቴር ተራ በደረሰ ጊዜ የሴቶች ጠባቂው የንጉሡ ጃንደረባ ሄጌ ከሚለው በቀር ምንም አልፈለገችም ነበር፤ አስቴርም በሚያዩአት ሁሉ ዓይን ሞገስ አግኝታ ነበርና።”— አስቴር 215

 

3.  ሩት- ከሞአብ ምድር አማችዋን ኑሐሚንን ተከትላ ወደ እስራኤል የገባች

ሞዓባዊቱም ሩት ኑኃሚንን፦ በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ተከትዬ እህል እንድቃርም ወደ እርሻ ልሂድ አለቻት። እርስዋም፦ ልጄ ሆይ፥ ሂጂ አለቻት።” — ሩት 22

 

4.  ነህምያ- በግዞት አገር ጠጅ አሳላፊ የነበረ

ንጉሡንም፦ ንጉሡን ደስ ቢያሰኝህ፥ ባሪያህም በፊትህ ሞገስ ቢያገኝ፥ እሠራው ዘንድ ወደ ይሁዳ ወደ አባቶቼ መቃብር ከተማ ስደደኝ አልሁት።” — ነሀምያ 25

 

5.  ዳንኤል- በግዞት ምድር እንጀራ አበዛ የነበረ

ንጉሡም ዳንኤልን ከፍ ከፍ አደርገው፥ ብዙም ታላቅ ስጦታ ሰጠው፥ በባቢሎንም አውራጃ ሁሉ ላይ ሾመው፥ በባቢሎንም ጠቢባን ሁሉ ላይ ዋነኛ አለቃ አደረገው።”— ዳንኤል 248

 

ሞገስ በዳንኤል ላይ፣ በግዞት አገር፦

1. ከፍ ከፍ አደረገው

2. ብዙም ታላቅ ስጦታ ሰጠው

3. በአገሪቱ ሁሉ ላይ ሾመው

4. በጠቢባን ሁሉ ላይ ዋነኛ አለቃ አደረገው

በማረኩአቸውም ሁሉ ፊት ሞገስን ሰጣቸው።” — መዝሙር 10646

 

መጨረሻም፦

ስለዚህ እድገታችን ላይ በእጅጉ ትኩረት ልናደርግ ይገባል። ለማንኛውም ነገራችን "በሞገስ" በሁሉ ፊት ማደግ ይሁንልን። የእግዚአብሔር ቃል እንደሚለው፦

1- ጌታችን ኢየሱስ

ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።” — ሉቃስ 252

2- ነቢዩ ሳሙኤል

ብላቴናውም ሳሙኤል እያደገ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም በሰውም ፊት ሞገስ እያገኘ ሄደ።” — 1 ሳሙኤል 226

 

ተባረኩ

መምህር በረከት ሱላሞ ሱጌቦ

+251902910126