yegizewkal
ቃልህ ተገኝቶአል እኔም በልቼዋለሁ አቤቱ፥ የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ። ትንቢተ ኤርምያስ 15፥16

  • Home/መነሻ ገጽ
  • Gospel Thoughts/የወንጌል አስተምህሮ
    • ነገረ ድነት/Salvation
  • The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
    • Literature/ስነ-ጽሑፍ
    • ከመጽሐፍት ዓለም
  • Churches/ቤተ ክርስቲያን
    • Religious News/ሐይማኖታዊ ዜና
  • Testimony/ምስክርነት
  • ማስታወቂያ/Advertisement
  1. You are here:  
  2. Home

Home/መነሻ ገጽ

የእግዚአብሔር ምሪት

Details
Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ

ማቴ. 1፡18 የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። 19 እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ። 20 እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፥ እንዲህም አለ፦ የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፥ ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ። 21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።

Read more: የእግዚአብሔር ምሪት

በፍቅር ተመላለሱ

Details
Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ

የሰው ማንነቱ በምልልሱ ይታወቃል። የምንመላለስበት አካሄድ ደግሞ የመሆናችንና የሆነውን የመረዳታችን ውጤት ነው። ወደ ፊልሞና
1፥6 "የእምነትህም ኅብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ፤"  ወደ ኤፌሶን ሰዎች
1፥17 "የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።"

Read more: በፍቅር ተመላለሱ

በጌታ ደስ ይበላችሁ

Details
Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ

በጌታ ደስ ይበላችሁ ሲል ለምን እንዳለ ማወቁ በጣም ይረዳናል። ሰዎች የሚደሰቱት "ይህ አለን" ብለውና ይህን ያላቸውን ነገር በማሰብና በማሰላሰል ነው። ነቢዩ እንባቆምን በጽሑፉ ስናየው በህይወቱ ሲያስደስቱት የነበሩ ነገሮች ነበሩ። እነዚህ የሚያስደስቱት ነገሮች ከህይወቱ በጎደሉ ጊዜ የሚደሰትበትን ነገር ሲያስብ ጎድሎበት አየ። በዚህ ጊዜ ነው አንድ ከሁሉ በላይ ሊታሰብ የሚገባውን ነገር የተረዳው፤ ይኸውም እግዚአብሔር። ይህ እግዚአብሔር ወገኑ መሆኑን ሲረዳና ሲያስብ ደስታውም ደስታውም በእርሱ መሆኑን ተረዳው። ይህ እግዚአብሔር ለእንባቆም የመድኃኒቱ አምላክ ነበር። 

የእግዚአብሔር ስም የጸና ግምብ ነው

Details
Category: The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ

መጽሐፈ ምሳሌ 18፥10 የእግዚአብሔር ስም የጸና ግምብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል።

የእግዚአብሔር ስም ለሚታመኑት በከፍታ እንደተሰራ የመጠከለያ ግንብ ነው። ጠላት ያለውን ሁሉ ቢወረውር በዚህ ስም የተከለለውን ሊነካው አይችልም። ስሙ የጸና ግምብ ነው።

በከፍታ ስፍራ እንደተቀመጠ ሰው በዚህ ስም የተደገፈ ሁሉ እንደዚሁ በከፍታ ስፍራ ሆኖ ይጠበቃል። የጻድቅም ተስፋው የእግዚአብሔር ስም ነው። ጻድቅ ሁልጊዜ የሚሮጠው ወደዚህ ስም ነው።

 

Page 3 of 4

  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • የአንደኛ ዮሐንስ መልዕክት
  • የአንደኛ ዮሐንስ መልዕክት
  • ጊዜ
  • ትጋት
  • ሐሰት፣ ሐሰተኛ፣ ሐሰተኝነት እና መገለጫቸው

Article Categories

  • Literature/ስነ-ጽሑፍ
  • Gospel Thoughts / የወንጌል አስተምህሮ
  • The Feast of the Word/ከቃሉ ማዕድ
  • Testimony/ምስክርነት
  • Religious News/ሐይማኖታዊ ዜና
  • Churches/ቤተ ክርስቲያን

Login Form

  • Forgot your password?
  • Forgot your username?
Copyright © 2025 yegizewkal. All Rights Reserved.